የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የተፋሰስ መረጃ ክትትል ስትራቴጅክ ዕቅድ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያየ።
ግንቦት 04/2017 ዓ/ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የተፋሰስ መረጃ ክትትል እስትራቴጂክ ዕቅድ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር በሀዋሳ ከተማ ውይይት አደረገ።
በውይይት መርሃ-ግብሩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የክቡር ሚኒስትሩ አማካሪ ክቡር አቶ ሞቱማ መቃሳ ኢትዮጵያ የውሃ ሀብቷን በሚገባ ለመጠቀም የጎርፍ ፣የድርቅና የተለያዩ ችግሮች ማነቆ ሆነው መቆየታቸውን ጠቅሰው ለችግሮቹ መፍትሔ ለማምጣት የምክክር መድረኩ ወሳኝ ነው ብለዋል።
የውሃ ሀብት አስተዳደር ፋይዳ የሚለካው ለመህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች ጥራትን፣ መጠንንና ወቅቱን የጠበቀ የውሃ ሀብት አስተማማኝና ፍትሃዊ በሆነ አግባብ እንድኖር ማድረግ መሆኑን የገለጹት ክቡር አቶ ሞቱማ መቃሳ ለዚህም የመረጃ አያያዝና ክትትል ወሳኝ በመሆኑ ለስኬቱ ሁሉም ባለድርሻ አካል የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።
በመድረኩ ከ9 ዩኒቨርሲቲዎች የተጋበዙ ምሁራን ፣ አዲስ አበባና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ የክልሎች የውሃና ኢነርጂ ቢሮ ሀላፊዎዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እየተሳፉ ነው።
መርሃ ግብሩን በሚመለከት በቀረቡ የተለያዩ ጽሑፎች ላይ ተሳታፊዎች ተወያይተውበታል።