አመታዊ የውሃ ምርምር ላይ ያተኮረ ሲምፓዝየም እየተካሄደ ነው።

አመታዊ የውሃ ምርምር ላይ ያተኮረ ሲምፓዝየም እየተካሄደ ነው። ሚያዚያ 23/2017 ዓ/ም (ው.ኢ.ሚ) ዓመታዊ የውሃ ምርምር ላይ ያተኮረ ሲምፓዝየም እየተካሄደ ነው። የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስቴትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ በሲምፓዝየሙ ላይ ተገኝተው በውሃ ዘርፍ ላይ ለተሰማሩ ተመራማሪዎች እና ለተለያዩ አካላት መልዕክት አስተላልፈዋል ። የምርምር ተቋሞቻችን ከሳይንስ የዘለለ ተጨባጭ እና ችግር ፈች የሆኑትን የውሃ ተቋማት መለዋወጫ ፣ የውሃ ቆጣቢ ቴክኖሎጂዎችን ማምረት ፣ በኃይል ምክንያት አገልግሎት እንዳይቋረጥ የሶላር ቴክኖሎጂዎች መፍጠር ይገባል ሲሉ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ ገልፀዋል ። ክብር ሚኒስትሩ አያይዘውም የምርምር ማዕከሎች መፍትሔ አመንጭ የፖሊሲ ምክረ ሀሳብ በማቅረብ የልቀት ማዕከል ሆነው እንዲያገለግሉ ከሚኒስቴሩ እና ከኢንስቲትዩቱ ጋር ተቀናጅተው መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል። ክቡር ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ግቢ የተሠሩ የተግባር ተኮር የቴክኖሎጂ ማሰልጠኛ ፓይሌቶችን ጎብኝተዋል። የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የክቡር ሚኒስትሩ አማካሪ አቶ ሞቱማ መቃሳ የምክክር መድረኩ በሳይንስ ፣ በፈጠራ እና በባለድርሻ አካላት መካከል ጠንካራ የእውቀት ሽግግርና ትብብርን ይፈጥራል ብለዋል። በሀገራችን በአየር ንብረት ለውጥ፣ በከተሞች መስፋፋት እና በተፈጥሮ ሀብት መራቆት ምክንያት በኢኮኖሚና ማህበራዊ እድገት ላይ የሚያስከትለውን ተግዳሮት በምርምር ላይ የተመሰረተ የመፍትሔ ሀሳብ ማቅረብ ከኢንስቲትዩቱ ይጠበቃል ብለዋል። የኢትዮጵያ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዋና ዳርክተር ዶ/ር ታመነ ሀይሉ በበኩላቸው ተቋሙ እደዚህ አይነት በምርምር እና ኢኖቬሽን ላይ የተመሠረተ ስምፖዝየም ሲያዘጋጅ የመጀመሪያው መሆኑን ገልፀው ፤ እያደገ የመጣውን ቴክኖሎጅ የሚመጥን የሰው ኃይል ልማት ላይ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል። በቀጣይ የሴክተሩን አቅም ከመገንባት በተጨማሪ ኢንስቲትዩቱ ከዚህ በፊት ከ100 ያልበለጡ ሰልጠኞችን ተቀብሎ ሲያሰለጥ የቆየ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በአንድ ጊዜ ከ2500 በላይ ማስተናገድ መቻሉንም አክለው ገልጸዋል። በሲምፖዚየሙ የፌዴራል፣ የክልሎች ፣ የዩኒቨርስቲ እና የምርምር ተቋማት የዘርፉ ባለሙያዎች እና ተመራማሪዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ። በነገው እለትም በተለያዩ ክልሎች በተግባር የተደገፉ እና የተጠኑ የምርምር ውጤቶች ላይ ምክክር ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

Share this Post