በተሻሻለው ረቂቅ የውሃ ፖሊሲ ላይ በማኔጅመንት ደረጃ ውይይት ተደረገ፡፡
በተሻሻለው ረቂቅ የውሃ ፖሊሲ ላይ በማኔጅመንት ደረጃ ውይይት ተደረገ፡፡
ጥር 29/2017 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚንስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ በተመራ መድረክ በተሻሻለው ረቂቅ የውሃ ፖሊሲ ላይ በማኔጅመንት ደረጃ ውይይት ተደርጓል።
በውይይቱ ማስጀመሪያ ላይ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የክቡር ሚንስትር ጽ/ቤት ሀለፊ አቶ ማሙሻ ሀይሉ የፖሊሲ አዘጋጅ ኮሚቴን በመወከል የፖሊሲው ክለሳ ሂደሰት ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ስራው ጊዜ ተወስዶ በጥንቃቄ እንደተሰራ የገለፁት አቶ ማሙሻ ጠቃሚ ይሆናሉ ብሎ ኮሚቴው ያመነበትን የሌሎች ሀገራትን የውሃ ፖሊሲዎችን ለማመሳከር እንደተሞከረ ገልፀዋል።
የተዘጋጀውን የረቂቅ ፖሊሲውን ሰነድ ያቀረቡት አቶ በላይነህ ይርዳው በውሃ ሀብት አስተዳዳር ዘርፍ አማካሪ የረቂቅ ፖሊሲው አስፈላጊነት፣ መርሆዎችና ዓላማዎቹ ላይ ገለጻ አድርገዋል፡፡
አቶ በላይነህ ፖሊሲውን ማሻሻል ያስፈለገበትን ምክንያት፣ ከትግበራ በኋላ ሊታይ የሚችለው ውጤት ምን ሊሆን እንደሚችልና በውስጡ የተካተቱ ጉዳዮችን በመዘርዘር ሰፋ ያለ ገለጻ አድርገዋል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ረቂቅ ፖሊሲው ዓለም አቀፍ እስታንዳርድ መያዝ ስላለበት የዓለም ሀገራትን የውሃ ህጋዊ ማእቀፎችን ማጤንና ይገባል ብለዋል፡፡
ተወያዮቹ የውሃ ብክነትን ከመታደግ አንፃር የዝናብ ውሃ መጠቀምንና ውሃን በቁጠባ መጠቀምን እንደባህል ሆኖ እንዲቀጥል በህጉ ውስጥ ማመላከት ይገባል ብለዋል።