ኢትዮጵያና እስራኤል በውሃና ኢነርጂ ልማት ዘርፍ በትብብር ለመስራት ያላቸውን ፍላጎት ገለጹ፡፡
ጥር 27/2017 ዓ.ም. (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ በውሃ ሀብት ልማትና በኢነርጂ ልማት ዘርፍ ትብብር ላይ ትኩረት ያደረገ የፍላጎት መግለጫ ሰነድ ከእስራኤል የኢነርጂ እና መሰረተልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ሚ/ር ኢሊ ኮህን ጋር ተፈራርመዋል፡፡
በፊርማ ስነስርዓቱ ወቅት ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ የከርሰምድር ውሃ ፍለጋና ማውጣት ላይ፤ የፍሳሽ ማጣራት ቴክኖሎጂዎች ላይ እና በታዳሽ ሀይል ልማት ላይ በተለይ ፤ ከዋናው መስመር ርቀው በሚገኙ ገጠራማ አካባቢዎች ላይ የጸሃይ ሀይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ትግበራ ላይ የእስራኤል ተቋማት ሊሰማሩ የሚችሉባቸው ዘርፎች መሆናቸውን አንስተዋል፡፡
የእስራኤል የኢነርጂና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ሚ/ር ኢሊ ኮህን በሁለት መንገድ በትብብር መስራት እንደሚቻል ጠቅሰው፤ በአንድ በኩል በአቅም ግንባታ እና በእውቀት ሽግግር ላይ ከእስራኤል ድርጅቶች ጋር መስራት እንደሚቻልና በሌላ በኩል በግሉ ዘርፍ በውሃ ልማት ላይና በኢነርጂ ልማት ላይ የእሰርኤል ድርጅቶች ተሰማርተው ውጤት ማሳየጥ እንደሚችሉ ተናረዋል፡፡
በተፈረመው የትብብር ፍላጎት መግለጫ ሰነድ ውስጥ፤ አስተማማኝ የታዳሽ ሀይል ልማት ላ፣ የኦፍግሪድ ኢርጂ ልማት፣ የፍሰሽ አወጋግድ እና በአጠቃላይ በውሃ ሀብት እና ኢነርጂ ሀብት ልማት ኢኖቬሽን ላይ ትኩረት ያደረጉ ነጥቦች ተካተዋል፡፡