በሲዳማ ክልል በሐዋሳ ከተማ ዙሪያ በኤሌክትሪክ ኃይል መስኖን የሚያለማ ፕሮጀክት ለአገልግሎት ዝግጁ መሆኑ ተገለፀ።

በሲዳማ ክልል በሐዋሳ ከተማ ዙሪያ በኤሌክትሪክ ኃይል መስኖን የሚያለማ ፕሮጀክት ለአገልግሎት ዝግጁ መሆኑ ተገለፀ።

የካቲት/2016 ዓ/ም በሲዳማ ክልል በሐዋሳ ከተማ ዙሪያ በኤሌክትሪክ ኃይል መስኖን የሚያለማ ፕሮጀክት ለአገልግሎት ዝግጁ መሆኑ ተገለፀ።

በሲዳማ ክልል ጉብኝት ላይ ያሉት የኢነርጂ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ድኤታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ የተመራ ቡድን ከሰዓት በኋላ በሲዳማ ክልል በሐዋሳ ከተማ ዙሪያ በኤሌክትሪክ ኃይል መስኖን የሚያለማ ፕሮጀክት በጎበኙበት ወቅት በሲዳማ ክልል ኤሌክትሪክ ኃይል በመጠቀም መስኖን ለማልማት እየተደረገ ያለው ጥረት አድንቀው፤ አለም አቀፍ የልማት ድርጅቶች በሶላር ኃይል መስኖን የሚያለማ ቴክኖሎጂ በማቅረብ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

ክቡር ሚኒስትር ድኤታው አያይዘውም የሶላር ኃይል መጠቀማችን ወጪ ከመቀነስ አንፃር፣ የውጭ ምንዛሪን ከማዳን፣ የአከባቢ ብክለት ለመቀነስና የነዳጅ ጥገኝነትን የማስወገድን ጨምሮ የሶላር ኃይል መጠቀም ብዙ ችግሮችን ይፈታል ብለዋል።

የሲዳማ ክልል ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊው ዶ/ር ከበደ ጋኖሌ በበኩሉ በሸበዲኖ ወረዳ የተሰራው መስኖን የሚያለማ የሶላር ኢነርጂ ወደዚህ አምጥተን መጠቀም ብንችል የበለጠ አርሶአደሮችን ተጠቃሚ ማድረግ ያስችለናል ብለዋል።

ኃላፊው ጨምረውም በጋሎ አርጌሳ ፕሮጀክቱ ከ135ሽህ ሄክታር በላይ መሬት የሚያለማ ሲሆን 82 ሚልየን ብር ወጪ የመስኖ መሠረተ ልማት ተዘርግቶ መጠናቀቁን ገልፀዋል።

Share this Post