በባዘርኔት ፕሮጀክት በአዋሽ ተፋሰስ ሊሰሩ በተመረጡ ሳይቶች ዙሪያ ጉብኝት መካሄዱ በቀጣይ ተግባራት ትልቅ ግብዓት ይሆናል-አቶ ሞላ ረዳ የባዘርኔት ፕሮጀክት አስተባባሪ

በባዘርኔት ፕሮጀክት በአዋሽ ተፋሰስ ሊሰሩ በተመረጡ ሳይቶች ዙሪያ ጉብኝት መካሄዱ በቀጣይ ተግባራት ትልቅ ግብዓት ይሆናል-አቶ ሞላ ረዳ የባዘርኔት ፕሮጀክት አስተባባሪ አፋር ሰመራ-ታህሳስ 2018 ዓ.ም.(ው.ኢ.ሚ) በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በባዘርኔት ፕሮጀክት በአዋሽ ተፋሰስ በተመረጡ ሳይቶች ዙሪያ ጉብኝት መካሄዱ በቀጣይ በተቀናጀ ውሃ ሃብት አስተዳደር ለሚሰሩ ተግባራት ትልቅ ግብዓት እንደሚሆን የተናገሩት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የባዘርኔት ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ሞላ ረዳ ገለጹ፡፡   አስተባባሪው አክለውም ከጉብኝቱ አንድ ቀን ቀደም ብሎ በአዋሽ ተፋሰስ ነባራዊ ሁኔታ የግምገማ ሪፖርት ማረጋገጫ አውደ ጥናት ቀርቦ በባለድርሻ አካላት ውይይት የተደረገበት መሆኑን አስታውሰው ይህንን ውይይት ተከትሎም የተመረጡ ሳይቶች ጉብኝት እንዲካሄድ መደረጉን አስታውሰው የተመረጡ ሳይቶች ለተቀናጀ ውሃ ሃብት አስተዳደር ምቹ መሆናቸውን ለመለየትና የአካባቢውን አርብቶ አደር ችግሮች ለመገምገም እንዲቻል የመስክ ምልከታ ማድረግ አስፈልጓል ብለዋል፡፡   በተጨማሪም የባዘርኔት ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ዮሃንስ ዘሪሁን በበኩላቸው በመስክ በምልከታው ወቅት የተጎበኙት ሳይቶች ሲጠናቀቁ የከፊል አርብቶ አደሩንና የአርብቶ አደሩን ኑሮ ለማሻሻል ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥሩ፣ለከብቶች የግጦሽ መሬትን በማልማት ጉልህ ድርሻ እንደሚጫወቱና፣በተፋሰሶች ውስጥ የአፈርን እርጥበት ለማስጠበቅ የሚያስችል ጠቀሜታ እንዳላቸው አመልክተዋል፡፡   በቀጣይ የተቀመጡ አቅጣጫዎችን አስመልክቶ አቶ ሞላ ሲገልጹ ቅድሚያ መስጠት ባለብን ጉዳይ ላይ በማተኮር ለስራው ባለቤቶች የአቅም ግንባታ ስልጠና በመስጠት በታቀደ መልኩ ስራውን ወደ መሬት ለማውረድ ጥረት የምናደርግ ሲሆን ሁሉም ባለድርሻ ሃላፊነት ሊሰማው ይገባል ብለዋል፡፡ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተቀናጀ የውሃ ሃብት አስተዳደር ስራ አስፈጻሚ፣የባዘርኔት ፕሮጀክት አስተባባሪዎችና፣እንዲሁም የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና የክልል የዘርፉ ባለሙያዎች በጉብኝቱ ላይ ተሳትፈዋል፡፡

Share this Post