በኔፕ-አዴሌ ፕሮጀክት ትግበራ መመሪያ እና በአካባቢ ጥበቃ አስተዳደር ስርአት ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ፡፡
ጥቅምት14/2018 ዓ/ም (ው.ኢ.ሚ) የብሔራዊ የኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራም አካል የሆነው የአዴሌ ፕሮጀክት (Access to Distributed Electricity and Lighting in Ethiopia (ADELE) Project) አተገባበር ዙሪያ ከክልሎች ፣ዞኖች እና ወረዳዎች ለተወጣጡ ባለሙያዎች በአዋሽ ስልጠና ተሰጠ፡፡
የስልጠና መርሀግብሩን በንግግር ያስጀመሩት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሡልጣን ወሊ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የብሔራዊ ኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራም ትግበራን ለማሳለጥ ፕሮጀክቱን ለሚተገብሩ እና ለባለድርሻ አካላት የተለያዩ ቴክኒካል እና የአቅም ግንባታን ስራዎችን በማከናወን የኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራሙን ትግበራ ለማሳለጥ አቅምን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን አንስተው፤ ስልጠናው የዚሁ አካል መሆኑን ገልጸዋል።
ሚኒስቴር ዲኤታው በማያያዝ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሚተገበሩት ተግባራት አንዱ ለሆነው በጣም ገጠራማ ለሆኑ አከባቢዎች/Deep Rural areas/ በውጤት ተኮር የገንዘብ ድጎማ/Result Based Finance Grant/ የቤተሰብ ሶላር ሆም ሲስተም/Solar Home System/ በገጠር ላሉት የማህበረሰብ ክፍሎች ለማሰራጨት ቅድሚያ መዘጋጀት ካለባቸው ሰነዶች ውስጥ የፕሮጀክቱን የማስፈጸሚያ ማኑዋል (Specific Operational Manual) ላይ እና የአካባቢ እና ማህበራዊ ማኔጅመንት ስርዓት እና (Environmental and Social Management System) ተዘጋጅቶ በትግበራ ላይ እንደሚገኙና ፕሮጀክቱ በዋናነት በክልሎች የሚተገበር በመሆኑና በተዘጋጁት ሰነዶች ላይ ስልጠና መስጠት አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።
ለክልል ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊዎች፣ ለክልል፣ ለዞን እና ወረዳ ተወካዮችን በፕሮጀክቱ አተገባበር እና የአካባቢ እና የማህበረሰብ አስተዳደር ስርአት መመሪያ ዙሪያ ስልጠና ለሁሉም ክልሎች በመሰጠት እንዳለሞ ክቡር ሚኒስትር ዲኤታው ገልጸዋል።
ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው በማያያዝ በዚህ ከዚህ በፊት ስንጠቀምበት የነበረውን የማገዶ እንጨት የነበረ ሲሆን ያደግሞ የደን መጨፍጨፍ የአፈር መሸርሸር ስለሚያመጣ የግብርና ምርትና ምርታማነትን በመቀነስ የምግብ ዋስትና እንዳናረጋግጥ ያደረገ፣ የሴቶችና ህጻናት ለተለያዬ ለጤና ችግሮች የሚያጋልጥ እና የአየር ንብረትን ለውጥን ማያመጣ ስለሆነ አሁን ላይ በተለየ መልኩ ደግሞ ለኮምፖነንት 3 (component 3) ሶላር ሆም ሲስተም የተዘጋጀውን የአካባቢና ማሕበራዊ አስተዳደር መተግበሪያ (ESMS) ሰነድ ላይ ሰፊ ትኩረት በማድረግ ስልጠናው ይሰጣል ብለዋል።
ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው በመጨረሻም የተዘጋጀውን ስልጠና በአግባቡ በመከታተል እየተተገበረ በሚገኘው የብሔራዊ ኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራም የድርሻችሁን ኃላፊነት በመውሰድ ከሚመለከታቸው የመንግስት ድርጅቶች በዋናነት ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፣ ከትምህርት ቢሮና ከጤና ቢሮ እንዲሁም ከግል ሶላር አከፋፋዮች እና አሰራጮች በጋራ በመሆን ስራዎችን በጥራትና በአግባቡ እንድንተገብር ስልጠናው የሚያስገኘዉን ትልቅ ጥቅም በመረዳት፣ ተሳትፎ በማድረግ በኤሌክትሪፊኬሽን ዘርፍ የሚጠበቀው ውጤት እንዲመጣ የድርሻሁን እንድትወጡ አሳስባለሁ ብለዋል።
በስልጠናው የተገኙት የአፋር ክልል ውሃና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ አቶአህመድ ሻሚ ቢሮው ከለውጡ ቡሀላ በክልሉ ብዙ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ገልጸው በተለይ ከዋና መስመር ውጪ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ፕሮጀክቶች ቀርጾ እየተንቀሳቀሰ እና የኤሌክትሪክ ተደራሽ ለማድረግ የሚኒ ግራድ አሰራር ስርአት ዘርግቶ ለመተግበር እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ገልጰዋል።
በዚህ ስራ ላይ የውሃና ኢነርጂ ማኒስቴር ጋር ፕሮጀክቱን ለመተግበር ሁሉም ባለሙያ በትብብር በመስራት አስተዋጽኦ ማድረግ አለብን በማለት አቶ ከህመድ አሳስበዋል ።
በስልጠናው ላይ ከክልሎች ከዞኖችና ከወረዳ የኢነርጂ ቢሮ ባለሙያዎች እና የሚመለከታቸው አካላት የተሳተፋ ሲሆን ስልጠናው ለቀጣይ ሁለት ቀን በተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች ላይም እንደሚሰጥ ተገልጿል።