የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስቴር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ድንቁ ስዩም የስራ ርክክብ አደረጉ
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስቴር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ድንቁ ስዩም የስራ ርክክብ አደረጉ
ጥቅምት 24/2019 ዓ.ም(ው.ኢ.ሚ) በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር በክቡር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው የተሾሙት ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ድንቁ ስዩም የስራ ርክክብ አደረጉ።
በርክክብ ስነ ስርዓቱ ላይ በቀድሞው የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታነት ያገለገሉትና በአሁኑ ወቅት የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ በኃላፊነት ዘመናቸው ስለተከናወኑ ስራዎች፣ በሂደት ላይ ስላሉ ፕሮጀክቶችና ስለቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ሰፊ ገለፃ አድርገዋል።
ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ ባለፉት ዓመታት በዘርፉ የተሳኩ ስራዎች መከናወናቸውን ጠቅሰው፤ በተገኙት ውጤቶችም እጅግ ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀዋል።
ውሃ፣ ግብርናና መስኖ እርስ በርስ የተሳሰሩና የማይነጣጠሉ ዘርፎች መሆናቸውን ያነሱት ክቡር ሚኒስትሩ በኢነርጂ ልማት ዘርፍም በኤሌክትሪፊኬሽን፣ በገጠር ኢነርጂ ቴክኖሎጂና በኢነርጂ ሀብት ጥናት የተጀመሩ ስራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አሳስበዋል።
በተለይም የገጠር ኤሌክትሪፊኬሽን ፕሮግራምን በቀጣይ ለማጠናከር ከልማት አጋሮችና ከለጋሽ ተቋማት ጋር ያለውን ትብብር ማጠናከርና ከባለሙያዎች ጋር በቅንጅት መስራት አስፈላጊ መሆኑንም ጠቁመዋል።
ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው በዘርፉ የተጀመሩ ስራዎችና የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች፣ እንዲሁም የህብረተሰቡን ጥያቄ በአግባቡ ለመመለስ የተጀመሩ የፖሊሲ ማሻሻያዎች በአመራር ሽግግሩ ሳይስተጓጎሉ በተሻለ መንገድና ፍጥነት መቀጠል እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
የተረከቡትን ሀገራዊ ኃላፊነት በብቃት በመወጣትና ዘርፉን ወደ ተሻለ የልማት ደረጃ ለማሸጋገር በትጋት እንዲሰሩም ክቡር አሳስበዋል።
በትውውቅና በስራ ርክክብ ስነ ስርዓቱ ላይ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ልማት ዘርፍ አመራሮችና ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ድንቁ ስዩምም ስለቀረበላቸው ገለፃና የስራ ርክክብ አመስግነዋል።