የውሃ ሀብት አስተዳደርን ማጠናከር ለሁሉም መሰረተ ልማት ወሳኝ ነው ተባለ
የውሃ ሀብት አስተዳደርን ማጠናከር ለሁሉም መሰረተ ልማት ወሳኝ ነው ተባለ
ጥቅምት 06/2019 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የሚተገበረው (Basin scale Resilience Initiative for Ethiopia) የባዘርኔት ፕሮጀክት በላይኛው አዋሽ ተፋሰስ አደአ ወረዳ ላይ በ57 ሚሊዮን ብር ወጪ የገዋ-ወርቆ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ግንባታ ማስጀመሪያ መርሃግብር ላይ የውሃ ሀብት አስተዳደርን ማጠናከር ለሁሉም መሰረተ ልማት ወሳኝ መሆኑን አቶ ሞቱማ መቃሳ ገለፁ።
በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የክቡር ሚኒስትሩ አማካሪ ክቡር አቶ ሞቱማ መቃሳ በፕሮጀክቱ የሚተገበሩ የተፋሰስ ስራዎችን ማጠናከርና ህብረተሰቡን የንፁህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ለማድረግ በአካባቢው በብራይት ፕሮጀክት በርካታ የልማት ስራዎች እየተተገበረ መሆኑንም ጠቁመዋል።
የመስኖም ሆነ የኢነርጂ ልማት መነሻው ውሃ ሲሆን መገኛውም በተፋሰሱ ውስጥ ነው ያሉት ክቡር አቶ ሞቱማ ተፋሰሱን ካልጠበቅን ለመሰረተ ልማት የሚውለውን ውሃ ማግኘት ስለማይቻል ተፋሰስን መሰረት ያደረጉ ልማቶች ላይ ትኩረት ማድረግ ይገባል ብለዋል።
በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የባዘርኔት ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ሞላ ረዳ በበኩላቸው ፕሮጀክቱ ካሉት አምስት ዓላማዎች መካከል አንዱ ንፁህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ሲሆን በአዋሽና በዋቢሸበሌ ተፋሰስ በተመረጡ ሳይቶች ላይ ንፁህ የመጠጥ ውሃን ለማህበረሰቡ ማዳረስና ህብረተሰቡ በመስኖ ልማት ስራዎች ራሱን እንዲችል የተፋሰስ እንክብካቤና የመስኖ ልማት ስራዎችን እያስፋፉ መሆኑን ጠቁመዋል።
አቶ ሞላ አክለውም ከብራይት ፕሮጀክት ጋር በጋራ የተፋሰስ ልማት ስራ፣ የድጅታላይዜሽን፣ የቤዚን ኢንፎርሜሽን እና የላይቪሊሁድ ስራዎችን እየተሰሩ መሆኑን ጠቁመው፤ የገዋ-ወረቆ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ ለ15 ዓመታት አገልግሎት መስጠት የሚችል ነው ብለዋል።
የአደአ ወረዳ አስተዳደር ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ እሸቱ ጎሳዬ ውሃን መሰረት ያደረጉ የልማት ስራዎች የተፈጥሮውን የምንጭ ውሃ ወደ ዘመናዊ የአጠቃቀም ዘዴ በመቀየር የአካባቢውን ህብረተሰብ ለመጠጥ፣ ለመስኖና ለእንስሳት አገልግሎት የሚሰጥ በመሆኑ ወረዳው ከህብረተሰቡ ጋር በጋራ ያለምንም ቀስቃሽ
በመጨረሻም በክቡር አቶ ሞቱማ መቃሳ የተመራው ቡድን በጉምቢቹ ወረዳ ቡኢ ደንገጎ ቀበሌ በውሃና መሬት ሀብት ማዕከል በብራይት (BRIGHT)ፕሮጀክት የሚተገበረውን የመስኖ መቀልበሻ እና ቦይ (Wedecha Pickupweir and canal) ግንባታን ጎብኝተዋል፡፡
በብራይት ፕሮጀክት እየተተገበረ ያለው ስራ ነባሩን የመስኖ መቀልበሻ የሚተካ ሆኖ ከወዴቻ ግድብ በጉምቢቹ ወረዳ (ቢኢ ደንገጎ ቀበሌ)፣ በአደአ ወረዳ (ለከተባ እና ለጎዲኖ ቀበሌዎች) የመስኖ ውሃ ለማድረሰ የሚያስችል ሲሆን የተሻለ የውሃ አጠቃቀም እንዲኖር በማስቻል ተጨማሪ የመስኖ መሬት ወደ ልማት ማስገባት የሚችል በመሆኑ የመስኖ ውሃ አጠቃቀምን የሚያሻሽልና 150 ሄክታር መሬትን የሚያለማ መሆኑን በጉብኝቱ ወቅት ተገልጿል።