የታዳሽ ኢነርጂ ሀብት ለመጠቀም የሚያስችል የቴክኖሎጂ እና የፋይናንስ ተግዳሮቶች ላይ መስራት እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

የታዳሽ ኢነርጂ ሀብት ለመጠቀም የሚያስችል የቴክኖሎጂ እና የፋይናንስ ተግዳሮቶች ላይ መስራት እንደሚገባ ተገለጸ፡፡ ሚያዝያ 20/ 2015 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) በኢትዮጵያ እና ታንዛኒያ በታደሽ ኢነርጂ ኢንቨስትመንት እድሎች ላይ ለመምከር በአዲስ አበባ በተዘጋጀው መድረክ ላይ ንግግር ያደረጉት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ እንደገለጹት አፍሪካ የተፈጥሮ ሀብት ባለቤት መሆኗንና ለማሳያም በኢትዮጵያ እና ታንዛኒያ በታዳሽ ኢነርጂ ሀይል የማመንጨት ከፍተኛ አቅም እንዳላቸው ገልፀው የታዳሽ ኢነርጂ ሀብትን አምርቶ ለመጠቀም የሚያስችል የቴክኖሎጂ እና የፋይናንስ ተግዳቶች ላይ መስራት እንደሚስያፈልግ ተናግረዋል፡፡ ክቡር ሚኒስትሩ የመድረኩን ጠቀሜታ አስመልክተው እንደገለጹት የሁለቱ ሀገራት የጋራ ስብሰባ ኢንቨስተሮች፣ የፋይናንስ ተቋማት እና የባለድርሻ አካላት በታዳሽ ኢነርጂ ሀብት ያሉትን አቅሞች እና የልማት እድሎች እንዲረዱ በማድረግ በጋራ ለመስራት ታሳቢ ያደረገ መሆኑን አስታውቀው፤ የውይይት መድረኩ በእኛ ሀገር መዘጋጀቱ የታዳሽ ኢነርጂ አቅሞች እና የልማት እድሎች ለኢንቨስተሮች፣ ለኢንተርፕራይዞች እና ለፋይናንስ ተቋማት ለማስገንዘብ መልካም አገጣሚ ነው ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ በታዳሽ ኢነርጂ ልማት ላይ የተሰማሩ የግል ዘርፉ በስፋት ማሳተፍ ያሚያስችል የመንግስትና የግል ሴክተሮች አጋርነት (Public Private Partnership PPPs) የህግ ማዕቀፍ በመዘጋጀቱና የኢነርጂ ምርቶችን መሸጥ የሚያስችል ከጎሮቤት ሀገራት ጋር የሚያገናኝ የኃይል ማስተላለፊያ መሰረተ ልማት በመመቻቸቱ የግል ባለሀብቶች የተፈጠረውን አስቻይ ሁኔታ በመጠቀም መዋለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ክቡር ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ አያይዘውም የመገናኛ ብዙሃንም ሀገራችን ያላትን የታዳሽ ኢነርጂ አቅሞች እና የልማት እድሎችን በአለም አቀፍ ቋንቋዎች በመጠቀም ለአልሚ ድርጅቶችና ኢንቨስተሮች እንዲያስተዋውቁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ የምክክር መድረኩ ለሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት በታዳሽ ኢነርጂ ልማት ዙሪያ ለኢንቨስትመንት የተዘጋጁ የፕሮጀክት ሁኔታዎች፣ በታዳሽ ኢነርጂ ልማት የፋይናንስ አቅርቦትና የአገልግሎት አሰጣጥ በኩል ያለው የፋይናንስ ተቋማት ሁኔታዎች እና ምቹ የኢንቨስትመንት ሁኔታዎች ዙሪያ የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው።

Share this Post