534 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የሚገነባው የሆሳዕና ከተማ የሳኒቴሽን ፕሮጀክት ግንባታ ተጀመረ።
ሚያዚያ 29/2017 ዓ/ም (ው.ኢ.ሚ.) 534 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የሚገነባው የሆሳዕና ከተማ የሳኒቴሽን ፕሮጀክት ግንባታ ተጀመረ።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፕሬዝዳንት ክቡር ዶ/ር እንዳሻው ጣሰው እና የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ የሆሳዕና ከተማ የሳኒቴሽን ፕሮጀክት ግንባታ አስጀምረዋል።
የሳኒቴሽን ፕሮጀክቱ በውሃና ኢነርጂ ሚንስቴር አማካኝት ከጣሊያ መንግስት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ እና በክልሉ መንግስት በጀት የሚገነባ ነው፡፡