16ኛው የሰንደቅ ዓለማ ቀን በዓል በደማቅ ሁኔታ ተከበረ፡፡

16ኛው የሰንደቅ ዓለማ ቀን በዓል በደማቅ ሁኔታ ተከበረ፡፡ ጥቅምት 5/2016 ዓ.ም. (ው.ኢ.ሚ) 16ኛው የሰንደቅ ዓለማ ቀን በዓል በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የበላይ አመራሮችና ሰራተኞች በተገኙበት በሚኒስቴሩ ቅጥር ግቢ በተለያዩ ዝግጅቶች በደማቅ ሁኔታ ተከበረ፡፡ በዓሉ የሰንደቅ ዓለማችን ከፍታ ለሕብረብሔራዊ አንድነታችንና ሉዓላዊነታችን ዋስትና ነው በሚል መሪ ቃል ከጧቱ 2፡30 ጀምሮ በድምቀት የተከበረ ሲሆን የሀገር አንድነትንና የሀገር ፍቅርን በሚገልጹ የተለያዩ ሙዚቃዊ ቃናዎች መልዕክቶች ተላልፈዋል፡፡ ስለ ሰንደቅ አላማ ምንነት፤ ክብርና ትርጓሜ በተገቢ መንገድ በማስረጽ ለሀገራችን ሉዓላዊነት፤ ለነፃነት እና ለሰንደቃችን ክብር የተደረገውንና እየተደረገ ያለውን ተጋድሎ እውቅና በመስጠት ማክበር እና የጋራ መግባባት መፍጠር ሕብረብሐራዊ ወንድማማችነትና ሀገራዊ አንድነት ማፅናት የሚሉ የእለቱ የሰንደቅ ዓለማ ቀን አላማዎችን ገለፃ ተደርጓል፡፡ በተጨማሪም የኢትዮጵያን ዳር ድንበር የሚጠብቁ እና የሀገር ሉዓላዊነትን ለማስከበር መስዋዕት እየከፈሉ ለሚገኙ የመከላከያ ሰራዊታችን እና ሌሎች የጸጥታ አካላት እውቅና እና ክብር መስጠት እንደሚገባም የበዓሉ መልዕከት ያስገነዝባል፡፡

Share this Post