የኢነርጂ ሴክተር ሪፎርምና የፕራይም ፕሮጀክት አንድ(PRIME project 1)ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሄደ።
የኢነርጂ ሴክተር ሪፎርምና የፕራይም ፕሮጀክት አንድ(PRIME project 1)ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሄደ።
ሰኔ 28/2016ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር በጋራ በመሆን የኢነርጂ ሴክተር ሪፎርምና የPRIME project 1( Power Sector Reform, Investment and Modernization in Ethiopia) ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በስካይ ላይት ሆቴል አካሄዱ።
የፕራይም ፕሮጀክት ከአለም ባንክ በተገኘ አነስተኛ ወለድ የብድር ድጋፍ የሚተገበር ሲሆን የሀይል ማሠራጫ መስመሮችን በማዘመን፣ በሀይል ማስተላለፊያና ማሠራጫ መስመሮች ላይ ያለውን ችግር በመቅረፍ፣ አዳዲስ የሀይል ማስፋፊያዎችን በመትከል እንዲሁም አጠቃላይ የሀይል ሴክተሩን በማዘመን ዘላቂነት ያለው የኢነርጂ ተደራሽነትን ለማምጣት የሚጫወተው ሚና ላቅ ያለ ነው ተብሏል።
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ልማት ዘርፍ አማካሪ አቶ ጎሳየ መንግስቴ የሀይል ዘርፍ ማሻሻያን የተመለከተ ጽሁፍ አቅርበዋል።
በጽሁፉ እንደተመላከተው የኢትዮጵያ የሀይል ስርዓት እቅድ ማእቀፍ ስራን ከተቋም አንጻር በመገምገም ለመቆጣጠር መግባባት ላይ መደረሱ እና የመንግስትና የግል ሴክተሮች በዘርፉ ያላቸውን ሚና አስመልክቶ በእቅድ መካተቱን ይገልጻል።
በሀይል መስመር ዝርጋታ እና ማሻሻያ ላይ የሚስተዋሉ የአፈጻጸም ችግሮችን፣ ከሪፖርት አወቃቀር፣ ከተጠያቂነት ፣የአገልግሎት ጥራትን ከመለካት እና ሌሎች ተያያዠ ጉዳዮችን ለመዳሠስ የሚያስችል መግባባት ላይ መደረሡም በጽሁፉ ተመላክቷል።
የኢነርጂ ሪፎርሙን ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችል በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር እና በገንዘብ ሚኒስቴር በኩል አራት ንኡስ አባላት ያሉት የሪፎርም ግብረሀይል የተቋቋመ ሲሆን የኤሌክትሪክ ሀይልና ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋማት ደግሞ የአፈጻጸም እና የፋይናንሽያል ማሻሻያ እቅድ እያዘጋጁ መሆኑ በቀረበው ጽሁፍ ተካቷል።
በመርሃ ግብሩ የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ሰመሪታ ሰዋሰውን ጨምሮ ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ ከገንዘብ ሚኒስቴር፣ ከአለም ባንክ፣ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይልና ከኤሌክትሪክ አገልግሎት፣ ከኢነርጂና ነዳጅ ባለስልጣን እንዲሁም ከልማት አጋር ድርጅት የተወከሉ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል።