የታላቁ የኢትዮጲያ ህዳሴ ግድብ አፈፃፀሙ 95 በመቶ መድረሱ ተገለፀ፡፡

የታላቁ የኢትዮጲያ ህዳሴ ግድብ አፈፃፀሙ 95 በመቶ መድረሱ ተገለፀ፡፡

የካቲት /2016 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) ታላቁ የኢትዮጲያ ህዳሴ ግድብ 13ኛ ዓመት ክብረ-በአልን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ በተሰጠበት ወቅት አፈፃፀሙ 95 በመቶ መድረሱን የህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ፅ/ቤቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ፍቅርተ ታምር ገለፁ፡፡

የታላቁ የኢትዮጲያ ህዳሴ ግድብ በመላው ህዝባችን ተሳትፎና በመንግስት ቁርጠኝነት ክትትልና ድጋፍ አፈፃፀሙ 95 በመቶ መድረሱን የገለፁት ም/ዋና ዳይሬክተሯ፤ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የመሰረት ድንጋይ የተቀመጠበትን 13ኛ ዓመት በተለያዩ ዝግጅቶች ለማክበር በዝግጅት ላይ መሆናቸውንና እስከ 300 ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብ መታቀዱን ገልፀው ግድባችን በበርካታ ውጣ ውረዶች አልፎ በመደበኛና በህዝባዊ ዲፕሎማሲ ድሎች ታጅቦ፣ ከግንባታና ውሃ ሙሌት እሳቤ አልፎ ወደ ኃይል ማመንጨት ምዕራፍ ተሸጋግሮ፤ ላለፉት አራት ተከታታይ አመታት በአራት ዙር የውሃ ሙሌቶችን በስኬት በማጠናቀቅ ከ42 ቢሊዮን ሜትር ኪዩብ በላይ ውሃ በግድቡ እንደተያዘ አስታውሰዋል፡፡

ወ/ሮ ፍቅርተ አያይዘውም "በህብረት ችለናል" በሚል መርህ ቃል የሚከበረውን 13ኛ አመት በአል የቦንድ ሳምንት፣ የህዝብ ንቅናቄና የሀብት ማሰባሰብ ሁነቶች የበአሉ አካል ሲሆኑ ዜጎች እስከአሁን ድረስ ላደረጉት አስተዋፅኦ የምስጋናና የእውቅና ስነስርአትም እንደሚካሄድ ጠቁመዋል፡፡

በመድረኩ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ምክር ቤት አባላት፤ የሀይማኖት አባቶች፤ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፤ የወጣት ማህበራት አመራሮች ቀሪ ስራዎችን ለማጠናቀቅ ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

Share this Post