የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በሀገራዊ ማክሮ ኢኮኖሚ እድገትና የተቋሙ የ9ወር እቅድ አፈጻጸም ዙሪያ ውይይት አካሄደ፡፡

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በሀገራዊ ማክሮ ኢኮኖሚ እድገትና የተቋሙ የ9ወር እቅድ አፈጻጸም ዙሪያ ውይይት አካሄደ፡፡ ግንቦት 17/2015ዓም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በማክሮ ኢኮኖሚ ሀገራዊ ጥቅል እድገት፣ በተቋሙ የ9 ወር ስራ አፈፃፀም እና ቀጣይ የስራ አቅጣጫ ላይ ውይይት አካሄደ፡፡ በመድረኩ በማክሮ ኢኮኖሚ እድገት ላይ የተዘጋጀውን ሰነድ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ሱልጣን ወሊ ያቀረቡ ሲሆን፤ በሰነዱ በማክሮ ኢኮኖሚ እድገትና ተግዳሮቶች ዙሪያ፤ በተለይ የስራ እድል ፈጠራ፣ በሀገር ውስጥ ምርት እድገት፣ የፌደራል መንግስት ገቢና ወጪ፣ ተተኪ ምርቶች፣ የዋጋ ግሽበት፣ ሬሜታንስ፣ ፋይናንስ፣ የውጭ ንግድ መቀነስ ዋና ዋና ምክንያቶች እና ትኩረት በሚሹ ጉዳዬች ተካቶ ቀርቧል፡፡ በሌላ በኩል የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የ9 ወር እቅድ አፈጻጸምና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ሪፓርት በሚኒስቴር መ/ቤቱ የስትራቴጅክ ጉዳዮች ስራ አስፈጻሚ በአቶ አለሙ መንገሻ የቀረበ ሲሆን፤ ባለፉት 9ወራት የተከናወኑ ስራዎችን ማለትም፤ ከአስተዳደርና ስራ አመራር ዘርፍ፣ ከኢነርጂ ልማት ዘርፍ፣ ከውሀ ሀብት አስተዳደር እና ከመጠጥ ውሀና ሳኒቴሽን ዘርፎች አንጻር የተከናወኑ ተግባራት እና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን አካታው አቅርበዋል፡፡ ሰነዶቹ ከቀረቡ በኋላ በተሳታፊዎች በኑሮ ውድነት ላይ እንዲሁም ሌሎች ተቋማዊ ጉዳዮች ላይ ሀሳብ አስተያት የቀረበ ሲሆን፤ በክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ፣ በክቡር አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ እና በክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሡልጣን ወሊ ምላሽ ተሰጥቶበትና አጠቃላይ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና የተጠሪ ተቋማት የቀጣይ አቅጣጫ ተቀምጦ ስብሰባው ተጠናቋል፡፡

Share this Post