ከ 563 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ የውሃ ተቋማት ቁሳቁሶች አቅርቦት ውል ተወሰደ፡፡

ከ 563 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ  የውሃ ተቋማት ቁሳቁሶች አቅርቦት ውል ተወሰደ፡፡

ጥቅምት 9/2016ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በድርቅና ጦርነት ለተጎዱ አካባቢዎች ለውሃ ተቋማት ጥገና ከ563 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ የሚገዙ የተለያዩ ቁሳቁሶችን ለማቅረብ ከአላዳር ካምፓኒና ከአግራባት ኮንስትራክሽንና ትሬዲግ ጋር የውል ስምምነት ተፈራረመ፡፡

የውል ስምምነቱ በሁሉም ክልሎች  በድርቅና ጦርነት ጉዳት ለደረሰባቸው አካባቢዎች የአጭር ጊዜ መፍትሔ ለመስጠት የተካሄደ ሲሆን አልሃዳር ካምፓኒ 86 ጥልቅ የውሃ ጉድጓድ ፓምፕ፣55 ጀኔሬተር እና መለዋወጫዎችን በ434,264,829 ብር ለማቅረብ ውል ስምምነት  የወሰደ ሲሆን አግራባት ኮንስትራክሽንና ትሬዲግ ደግሞ የውሃ ቧንቧና ፊቲንጎችን  በ128,956,806 ብር ለማቅረብ የውል ስምምነት ወስዷል፡፡

ስምምነቱን የተፈራረሙት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ ስምምነቱ በድርቅና ጦርነት ለተጎዱ አካባቢዎች የተበላሹና አገልግሎት የማይሰጡ የውሃ ተቋማትን በመጠገን አስቸኳይ መፍትሔ ለመስጠት እጅግ ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡

ሁለቱ ድርጅቶች ባለፈው ዓመት በተመሳሳይ ችግር ውስጥ ለነበሩ አካባቢዎች የውሃ ተቋማትን ለመጠገን የሚያስችሉ ቁሳቁሶችን በተባለው ጊዜ ያቀረቡ ናቸው ያሉት አምባሳደሩ በቀጣይም በገቡት ውለታ  መሰረት  በማቅረብ ውጤታማ ስራ እንደሚሰሩ እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡  
ሁለቱም ድርጅቶች ቅሳቁሶችን በስልሳ ቀናት ውስጥ ለማቅረብ  ስምምነት አድርገዋል፡፡

Share this Post