በ22 ወረዳዎች ያሉ መካከለኛ የውሃ ተቋማት አገልግሎታቸውን ዘላቂ ለማድረግ የሚያስችል የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ፡፡

በ22 ወረዳዎች ያሉ መካከለኛ የውሃ ተቋማት አገልግሎታቸውን ዘላቂ ለማድረግ የሚያስችል የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ፡፡ ግንቦት 5/2017 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) በ9 ክልሎችና አንድ ከተማ አስተዳደር በ22 ወረዳዎች በGreen Climate Fund (GCF) ያሉ መካከለኛ የውሃ ተቋማት አገልግሎታቸውን ዘላቂ ለማድረግ የሚያስችል የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ፡፡ ስልጠናውን ያስጀመሩት በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ታምሩ ገደፋ የመጠጥ ውሃ አቅርቦትን በገጠርና በከተማ ተደራሽ ለማድረግ የGreen Climate Fund (GCF) ፕሮጀክትን በ 9 ክልልሎችና በድሬ ዳዋ ከተማ መስተዳድር ስር በሚገኙ 22 ወረዳዎች እየተተገበረ ነው ብለዋል፡፡ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከበግብርና ሚኒስቴር ጋር በጋራ ጥልቅና መካከለኛ የውሃ ጉድጓዶችን በመስራት እና የምንጭን ማጎልበት ተግባራትን በማከናወን አገልግሎት እንዲሰጡ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡ የውሃ ተቋማትን በመጠበቅ አገልግሎታቸውን ዘላቂ ለማድረግ አጋዥ የሆነው የአቅም ግንባታ ስልጠና ለባለሙያዎች መሰጠቱ በየወረዳው ላሉ የዋሽ ኮሚቴዎች ያገኙትን እውቀት በማጋራት የውሃ አገልግሎት ተቋማቱ እረጅም ጊዜ አገልግሎት እንዲሰጡና በቴክኖሎጂ የታገዘ ስራ እንዲሰራ ታሳቢ ተደርጎ ስለሆነ ተሳታፊዎች በንቃት መሳተፍ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡ ስልጠናው በኢትዮጵያ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢኒስቲቲዩት እየተሰጠ ሲሆን ከግንቦት 05/2017 አስከ ግንቦት09 /2017 ዓ.ም እንደሚቀጥልም ማወቅ ተችሏል፡፡

Share this Post