የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የመሠረት ድንጋይ የተቀመጠበት 13ኛ ዓመት ክብረ በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት ተከበረ።
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የመሠረት ድንጋይ የተቀመጠበት 13ኛ ዓመት ክብረ በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት ተከበረ።
መጋቢት/2016ዓ.ም (ው .ኢ.ሚ) የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የመሠረት ድንጋይ የተጣለበት ክብረ በዓል" በህብረት ችለናል" በሚል መርህ በህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት በደመቀ ሁኔታ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከበረ።
በክብረ በዓሉ የኢፊድሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ የሀይማኖት አባቶችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመውበታል።
በክብረበዓሉ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን የ13 ዓመታትን ጉዞ የሚያሳይ ኤግዚቢሽን በኢፌድሪ ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ተመርቆ ለእይታ ክፍት ሆኗል። እንዲሁም በኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት የተዘጋጀ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ማስታወሻ ቴምብርም ተመርቋል።