የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ለከተሞች ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤቶች 13 የሞተር ሳይክል ድጋፍ አደረገ።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ለከተሞች ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤቶች 13 የሞተር ሳይክል ድጋፍ አደረገ።

የካቲት 4/2016 ዓ.ም የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ለከተሞች ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤቶች 13 የሞተር ሳይክል ድጋፍ አደረገ።

የሞተር ሳይክሎቹ በውሃ ልማት ፈንድ አማካኝነት ከፈረንሳይ ልማት ኤጀንሲ በተገኘው ድጋፍ 2.7 ሚሊዮን ብር ወጪ ተገዝቶ የቀረበ ሲሆን በውሃ ልማት ፈንድ የተመቻቸ ብድር ተገንብቶ አገልግሎት እየሰጡ ከሚገኙት የውሃ ተቋማት መካከል ለ13 የውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤቶች ለአቅም ግንባታ ድጋፍ መሰጠቱን በርክክቡ ወቅት የውሃ ልማት ፈንድ መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ዶጊሶ ጎና ገልጸዋል።

የከተሞቹ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ተወካዮች ከመጠጥና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ድኤታ ከክቡር አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ ቁልፍ ተረክበዋል።

Share this Post