እየተካሄደ በሚገኘው አመታዊ የባለብዙ ባለድርሻ አካላት ፎረም የኢነርጂ ልማት ዘርፍ በልዩ ልዩ ርእሰ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደርጓል።
እየተካሄደ በሚገኘው አመታዊ የባለብዙ ባለድርሻ አካላት ፎረም የኢነርጂ ልማት ዘርፍ በልዩ ልዩ ርእሰ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደርጓል።
በመጀመሪያው ቀን ከሰዓት በጀመረው የዘርፍ መድረክ የኢነርጂ ልማት ዘርፍ መድረክ ላይ በኢነርጂ ዘርፍ ተግባራዊ በሚደረጉ ፕሮጀክቶች ላይ ውይይት ተደረገ ።
በፎረሙ ላይ የኤሌክትርፍኬሽን ጥናት፣ በአደሌ ፕሮጀክት አተገባበር፣ ፕራይም ፕሮጀክት 1፣ ኢነርጂ ሴክተር ሪፎርምን በተመለከተ፣ ኢንቨስትመንት፣ ማዘመን የመሳሰሉት ላይ፤ እንዲሁም ክላይሜት ፕሮሚስ ፕሮጀክት1 ዙሪያ ትኩረት ያደረጉ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
በተለይ በክላይሜት ፕሮሚስ ፕሮጀክት ላይ ከአየር ንብረት እና ክሊን ኢነርጂ ተደራሽ ከማድረግ አንጻር ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።
ፕሮግራሙን ያወያዩት የውሀና ኢነርጂ ዘርፍ አማካሪ አቶ ጎሳዬ መንግስቱ ፎረሙ ከአጋዥ ድርጅቶች ጋር የምንሰራውን ስራ የምንገመግምበትና አቅጣጫ የምናስይዝበት በመሆኑ በተለይ ለኢነርጂ ዘርፍ ወሳኝነት እንዳለው ገልጸዋል።
በእለቱ ከፍተኛ ሀይል የማመንጨት እና የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ በተመለከተ ጽሁፍ ቀርቧል