እየተካሄደ በሚገኘው አመታዊ የባለብዙ ባለድርሻ አካላት ፎረም በመጠጥ ውሃ አቅርቦትና ሳኒቴሽን ዘርፍ በልዩ ልዩ ርእሰ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደርጓል።
እየተካሄደ በሚገኘው አመታዊ የባለብዙ ባለድርሻ አካላት ፎረም በመጠጥ ውሃ አቅርቦትና ሳኒቴሽን ዘርፍ በልዩ ልዩ ርእሰ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደርጓል።
በመጀመሪያው ቀን ከሰዓት በጀመረው የዘርፍ መድረክ የመጠጥ ውሃ አቅርቦትና ሳኒቴሽን ዘርፍ መድረክ ላይ የዋሽ አፈጻጸም ቅልጥፍና የሚያሰፍን የፋይናንስ ስትራተጂ ገለፃ ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።
የፋይናንስ ስትራተጂው አላማ ዘላቂ የፋይናንስ ስትራተጂ ስርዓት በመዘርጋት ውጤታማ የዋሽ አፈጻጸም ማምጣት እንደሚቻል ተገልጿል። የፋይናንስ ስትራተጂው ተግባራዊ መደረጉ የሀገር ውስጥ ፋይናንስ ማሰባሰብና ማንቀሳቀስ ፣ ነባር የዋሽ ኢንቨስትመንት ማሻሻል ፣ የግል አክተሮች እና የፋይናንስ ተቋማት በዘርፉ ላይ ንዋይ መዋላቸውን እንዲያፈሱ ለማነቃቃት እንደሚያስችል ገለፃ ተደርጓል።
በተጨማሪም የሳኒቴሽን አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ ሁሉን አቀፍ አቀራረብ መከተል እንደሚገባ የጥናት ግኝት ለተሳታፊዎች ገለፃ ቀርቧል።
ዩኒቨርሳል የውሃ አቅርቦት ማሳካት አለመቻል፣ በቂ የሳኒቴሽን አገልግሎት ማቅረብ አለመቻል እና የኢንቨስትመንት ወጪን መመለስ (መሸፈን) አቅም ውስንነት እንደተግዳሮት የተገለፀ ሲሆን፤ እነዚህን ችግሮች መቅረፍ የሚያስችሉ በሳኒቴሽን ዘርፍ በመንግስት አስተዳደር ውስጥ በሁሉም ደረጃ አለመደራጀት ፣ የተሟላ የሰው ኃይል አለመኖር፣ ውስን የፋይናንስ አቅርቦት እና የመሠረተ ልማት ውስንነቶች በምክንያትነት ተዘርዝረዋል።
በተጨማሪም በመድረኩ የዋሽ ዲጂታይዜሽን ላይ፣ የገጠርና የከተማ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ላይ ትኩረት ያደረጉ ጽሁፎች ቀርበዋል።