እየተካሄደ በሚገኘው አመታዊ የባለብዙ ባለድርሻ አካላት ፎረም በውሃ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ በልዩ ልዩ ርእሰ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደርጓል።
እየተካሄደ በሚገኘው አመታዊ የባለብዙ ባለድርሻ አካላት ፎረም በውሃ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ በልዩ ልዩ ርእሰ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደርጓል።
በመጀመሪያው ቀን ከሰዓት በጀመረው የዘርፍ መድረክ በውሃ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደር ፕሮግራም እና ፕሮጀክት ላይ፤ የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደር ፕሮጀክት ትግበራ የሀብት ማፈላለግ ስራዎችን በተመከለተ፤ የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደር ፕሮጀክት ሂደትና ለውጥን በተመለከተ፤ ድንበር ተሸጋሪ የውሃ ሀብት አስተዳደር ላይ በተለይ፣ ቀጠናዊ የውሃ ዋስትና ለማረጋገጥ የትብብር ዘዴዎች ላይ ትኩረት ያደረገ ጽሁፍ ቀርቧል፤
ሌላው በመድረኩ የቀረበው የማዉንት ኬኒያ ኢዋሶ የውሃ ትብብር ቀሚል የኬኒያ የውሃ ሀብት አስተዳደር ልምድ ቀርቧል፡፡
የተፋሰስ መረጃ ስርዓትን በተመለከተ፣ ማእከላዊ የተፋሰስ መረጃ ስርዓት ማደራጀትን በተመለከተ፣ በኢትዮጵያ የግድቦች ደህንነት ክትትልና ቁጥጥ አማራጮችን በተመከለተ እና የውሃ ሀብት በርከት ያሉ ጽሁፎች ከቀረቡ በኋላ ውይይት ተደርጎባቸዋል