ዜጎችን በመጠጥ ውሃ አቅርቦት፣ በኢነርጂ ተደራሽ ለማድረግ እና ጽዱ ሀገርንና አካባቢን ለመፍጠር የሁሉም ባለድርሻ አካላት ትብብርና ተሳትፎ ወሳኝ ነው።
ዜጎችን በመጠጥ ውሃ አቅርቦት፣ በኢነርጂ ተደራሽ ለማድረግ እና ጽዱ ሀገርንና አካባቢን ለመፍጠር የሁሉም ባለድርሻ አካላት ትብብርና ተሳትፎ ወሳኝ ነው።
ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ
ሐምሌ 04/2016 ዓ/ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከልማት አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር ''በተግዳሮት ፊት መጽናት'' በሚል መሪቃል ያዘጋጀው የባለብዙ ባለድርሻ አካላት መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
መድረኩን በንግግር የከፈቱት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ ዜጎችን በመጠጥ ውሃ አቅርቦት፣ በኢነርጂ አቅርቦት ተደራሽ ለማድረግ እና ጽዱ ሀገርና አካባቢ ለመፍጠር የሁሉም ባለድርሻ አካላት ትብብር ወሳኝ ነው ብለዋል።
ክቡር ሚኒስትሩ አያይዘውም እያደገ የመጣውን ልማት በመደገፍ እና በተግዳሮት ፊት በመጽናት ፍትሃዊ እና ዘላቂ የውሃና ኢነርጂ ልማት ተደራሽ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት ሁሉም ባለድርሻ አካላት አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በመድረኩ ላይ የክልል መንግስታት ፣ የልማት አጋሮች፣ የሲቪል ማህበራት፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ፣ የግል አልሚዎች እና ሌሎች በዘርፉ ላይ የተሠማሩ ባለድርሻ አካላት የተገኙ ሲሆን፤ በሴክተሩ ያሉ መልካም አጋጣሚዎች እና ተግዳሮቶች ላይ ለሁለት ቀናት እንደሚመክሩ ይጠበቃል።