የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከዩኢንዲፒ ጋር በመተባበር በኦሮሚያ ክልል ለሚገኙ የማገዶ ቆጣቢ ምድጃ አምራች ሴቶች ስልጠና እየሰጠ ነው።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከዩኢንዲፒ ጋር በመተባበር በኦሮሚያ ክልል ለሚገኙ የማገዶ ቆጣቢ ምድጃ አምራች ሴቶች ስልጠና እየሰጠ ነው።

ሀምሌ1/2016 ዓ.ም. (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከዩኢንዲፒ ጋር በመተባበር በኦሮሚያ ክልል ለሚገኙ የማገዶ ቆጣቢ ምድጃ አምራች ሴቶች ስልጠና እየሰጠ ነው።

በውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር የዩኤንዲ ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ይመስላል ተፈራ ስልጠናው በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ እና የማገዶ ቆጣቢ ምድጃ ማምረት ላይ ተሰማርተው እየሰሩ ላሉ ከ75 ሴቶች በላይ ለሆኑ ስራ ፈጣሪዎች የተዘጋጀ መሆኑን ገልጸው፤ ሰልጣኖቹ በተሰማሩበት መስክ በቂ እውቀት እንዲያገኙና ውጤታማ እንዲሆኑ ታሳቢ ያደረገ ነው ብለዋል፡፡

አቶ ይመስላል በማያያዝ በማገዶ ቆጣቢና በንጹህ ሀይል አቅርቦት ላይ ሴቶችን ተሳታፊ ማድረግ የሴቶችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫና ከመቀነስ ባሻገር የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ያግዛል ብለዋል፡፡

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል ውሀና ኢነርጂ ቢሮ የኢነርጂ ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ሶሬሳ በበኩላቸው ስልጠናው በክልሉ 22 ዞኖች የሚገኙ ሴት የስራ ፈጣሪዎች በተለያየ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ስልጠና የሚሰጥ መሆኑን አንስተው፤ ሰልጣኞች ከስልጠናው ለስራቸው ግብዓት ሆኖ የሚያገለግል እውቀት ስለሚያኙ በትኩረት መከታተል ይጠበቃል ብለዋል ።

አቶ ተስፋዬ ስራ ፈጣሪዎቹ እስከዛሬ ግንባር ቀደም በመሆን እየሰሩ መሆናቸውን አውስተው፤ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በቅርበት በመከታተል የገበያ ትስስር በመፍጠር ስራቸውን ማሳደግ እንዲችሉ ብድር ከማመቻቸት ጀምሮ የተለየ ድጋፍ ቢያደርግ ይበልጥ ተጠቃሚ ይሆናሉ ብለዋል፡፡

ከምእራብ አርሲ ዞን የመጡት የስልጠናው ተሳታፊ ወ/ሮ አስናቁ አሚሶ ስልጠናው የማገዶ ቆጣቢ ምድጃ ስራን ስራ ለማዘመንና የተሻለ ስራ ለመስራት ጠቃሚ መሆኑን አንስተው፤ የክልሉ አስተዳደር ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል፡፡መ

ስልጠናው ለተከታታይ 3 ቀናት የሚቀጥል ሲሆን ፤ በቀጣይ ሌሎች ክልሎችንም እንደሚያካትት ከአስተባባሪዎች መረዳት ችለናል፡፡

Share this Post