የአባይ ተፋሰስ ቤዚን ፕላን አተገባበር የመግባቢያ ስምምነት የፊርማ ስነስርዓት ተካሄደ፡፡

የአባይ ተፋሰስ ቤዚን ፕላን አተገባበር የመግባቢያ ስምምነት የፊርማ ስነስርዓት ተካሄደ፡፡

ሚያዝያ 03/2016 ዓ/ም (ው.ኢ.ሚ.) የአባይ ተፋሰስ ቤዚን ፕላን አተገባበር የመግባቢያ ስምምነት የፊርማ ስነስርዓት ከክልል የፕላንና ልማት ቢሮዎች ጋር ተደረገ።

የአማራ፣ የኦሮሚያ እና ቤንሻንጉል ጉሙዝ የውሀና ኢነርጂ ቢሮዎች፣ የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ቢሮዎች፣ የአካባቢ ጥበቃ ቢሮዎች ኃላፊዎችና ተወካዮች በተገኙበት የአባይ ተፋሰስ ቤዚን ፕላን አተገባበር የመግባቢያ ስምምነት የፊርማ ስነስርዓት ከክልል የፕላንና ልማት ቢሮዎች ጋር ተደርጓል።

በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የውሃ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር አብርሃ አዱኛ እና ክልሎችን በመወከል የፕላንና የልማት ቢሮ ሃላፊዎችና ተወካዮች መካከል የተፈረመው ስምምነት የተዘጋጀው የአባይ ቤዚን ፕላን ወደ መሬት ወርዶ እንደየ ሴክተሮቹ ተጨባጭ ሁኔታ ተግባራዊ ለማድረግ ወሳኝ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የቤዝን ፕላኑ አተገባበር አደረጃትና የአመራር ሂደትን በተመለከተ ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጓል፡፡ በውይይቱም በተለያዩ ተሳታፊዎች ሀሳብና አስተያየት የተሰጡ ሲሆን፤ በመጨረሻም ክቡር ዶ/ር አብርሃ አዱኛ የተፋሰስ ከፍተኛ ም/ር ቤት አደረጃጀትን አንስተው ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ በማብራሪያቸውም በተፋሰስ ከፍተኛ ምክር ቤት በአዋጅ የተቋቋመ እና በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የሚመራና የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የምክር ቤቱ ሴክሬታሪያት ሆኖ ሲያገለግል መቆየቱን ገልፀው፤ በክልሎች ደረጃ የክልል ርዐሰ መስተዳድሮች ኃላፊነት እንደሆነና የክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ ውክልና ቢሰጠው የተሻለ ይሆናል የሚል ፕሮፖዛል አቅርበው በተሳታፊዎች ተቀባይነት አግኝቷል።

በመድረኩ የአባይ ቤዝን ፕላን ጠቅለል ያለ ገለጻ የቀረበ ሲሆን፤ ከቤዝን ፕላኑ የተቀዱ የውሃ ምደባ እቅድ፣ የውሃ ጥራት ስራዎች እቅድ፤ የተፋሰስ ልማት እቅድ፣ የተፋሰስ መረጃ አስተዳደር እቅድ፣ የዌትላንድ ማኔጅመንት እቅድ የመሳሰሉት ሰነዶች ቀርበዋል፡፡

Share this Post