የአባይ ተፋሰስ ቤዚን ፕላን አተገባበር ፕላትፎርም ምስረታን አስመልክቶ ውይይት እየተደረገ ነው።

የአባይ ተፋሰስ ቤዚን ፕላን አተገባበር ፕላትፎርም ምስረታን አስመልክቶ ውይይት እየተደረገ ነው።

ሚያዝያ 3/2016 ዓ/ም (ው.ኢ.ሚ) የአባይ ተፋሰስ ቤዚን ፕላን አተገባበርን ፕላትፎርም ምስረታን አስመልክት ውይይት እየተደረገ ነው።

መድረኩን በንግግር የከፈቱት በሚኒስትር ድኤታ ማዕረግ የክቡር ሚኒስትሩ አማካሪ አቶ ሞቱማ መቃሳ እንደገለፁት የአባይ ቤዚን ከፍተኛ የህዝብ ብዛት እና የገፀ ምድር ውሃ ሀብት ያለው በመሆኑ ከኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታው አንጻር ትልቅ ትኩረት የሚሻ መሆኑን ገልጸዋል። ዘመናዊ የቤዚን ፕላን ዝግጅት በሀገራችን አዲስ ቢሆንም ከአለም ተሞክሮ ባገኘነው ልምድ እና የተፋሰስ ማስተር ፕላን ጥናት እና ተቋማዊ አደረጃጀት ለመፍጠር የተሠሩ ስራዎችን ውጤት ማስገኘቱን ገልፀዋል ።

የክቡር ሚኒስትሩ አማካሪ አያይዘውም በተፋሰሱ ውስጥ ያለውን የውሃ ሀብት በተጠቃሚዎች መካከል ሚዛናዊ የውሃ ስርጭት በመፍጠርና ዘላቂ የውሃ ሀብት አስተዳደር ስርዓት መዘርጋት ለሁለንተናዊ ልማት ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ገልፀው፤ የተፋሰስ ልማት በአንድ ተቋም ብቻ ውጤታማ ስለማይሆን የክልሎች ትብብር እና የባለድርሻ አካላት ንቁ ተሳትፎ የቤዚኑን እቅድ ወደ ተግባር መቀየር እንዲያስችል የዘርፉ ተዋንያን የድርሻውን ሚና እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

የአባይ ቤዚን ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ የወንድወሰን መንግሥቱ በበኩላቸው የአባይ ተፋሰሱ ካለው የቆዳ ስፋት፣ የህዝብ ብዛት እና አለም አቀፍ ባህሪ አንጻር ከሌሎች ተፋሰሶች በተለየ ትኩረት ያስፈልገዋል ብለዋል። ተፋሰሱ ከፍተኛ የመስኖ፣ የውሃ ኃይል ማመንጫ፣ የዓሳ ሀብት እና ሌሎች ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው የተፈጥሮ ሀብቶች እምቅ አቅም ያለው በመሆኑ በተቀናጀ እና ዘለቄታዊ ባለው መልኩ ማልማት ይጠበቅብናል ብለዋል።

የፅ/ቤት ኃላፊው አያይዘውም የትኛውም የኢኮኖሚያዊ ሆነ የማህበራዊ ልማቶች ያለ ውሃ ሀብት ውጤታማ ስለማይሆን የውሃ ዘርፉን ወደ ላቀ ደረጃ በማሳደግ የአካባቢውን ልማት ፈጣንና ዘላቂ ማድረግ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ይጠበቃል ብለዋል።

Share this Post