የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከአፍሪካ ልህቀት ማዕከል ጋራ በጋራ መስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከአፍሪካ ልህቀት ማዕከል በጋራ መስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

መጋቢት 5/2016 ዓ/ም የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከአፍሪካ ልህቀት ማዕከል በጋራ መስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ።

ከፊርማ ስምምነቱ በኋላ ለጋዜጣኞች ማብራሪያ የሰጡት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ በመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን፣ በውሃ ሀብት አስተዳደር እና በኢነርጂ ልማት ዘርፎች በጋራ መስራት የሚያስችል የአቅም ግንባታ በተቀናጀ መልኩ ከማዕከሉ ጋር ስምምነት መደረጉን ገልጸዋል። የአቅም ግንባታ በአገር በቀል ተቋም መካሄዱ በውጭና በሀገር ውስጥ የሚሰጡ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች በተቀናጀ መልኩ ለማስኬድ ማስቻሉ፣ ለስልጠናው የሚወጣውን የውጭ ምንዛሬን በማስቀረት እና ዘላቂ የስልጠና ተቋም እንዲፈጠር የሚያስችል መሆኑን ገልፀው ; በቀጣይ ከልህቀት ማዕከሉ ጋር የአቅም ክፍተቶችን ለመለየት በጋራ እቅድ ይሰራል ብለዋል።

የአፍሪካ ልዕቀት ማዕከል ፕሬዝዳንት አቶ ዛድግ አብረሃ በበኩሉ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የዲጂታል ኤግዚቢሽን ማዕከል ግንባታ እና ምቹ የስራ አከባቢ ለመፈጠር የግቢው ውበት ለመጠበቅ በተሰራው ሥራ የክቡር ሚኒስትሩን የአመራር ብቃት አድንቀዋል። የልህቀት ማዕከሉም ከኢትዮጵያ ተሻግሮ ለአፍሪካ ሀገራት የአመራር ልማት ፕሮግራም መጀመሩን ገልፀው; የተፈረመውን የመግባቢያ ስምምነት ወደ ድርጊት በመቀየር በየሴክተሩ ያለው የአመራር አቅም ክፍተቶችን ለማሟላት በቁርጠኝነት እንደሚሠሩ አቶ ዛድግ አብረሃ ተናግረዋል።

Share this Post