የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አመራሮች እና ሰራተኞች በሀገራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ አፈጻጸም ላይ ውይይት አካሄዱ ነው

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አመራሮች እና ሰራተኞች በሀገራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ አፈጻጸም ላይ ውይይት አካሄዱ ነው

መጋቢት 5/2016ዓ/ም የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አመራሮች እና ሰራተኞች በሀገራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ አፈጻጸም ላይ ውይይት አካሄዱ ነው።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የውሃ ሀብት አስተዳደር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር አብርሃ አዱኛ በሀገራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ አፈጻጸም በተመለከተ በዋና ዋና የኢኮኖሚ ሴክተሮች ያተኮረ ለተሳታፊዎች ገለፃ አቅርበዋል። ከኢኮኖሚ እና የማህበራዊ ዘርፎች እንድሁም በግብርና ፣ በኢንዲስትሪ ፣ አገልግሎት፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እና የመሠረተ ልማት ዝርጋታዎች ከ2012 ጀምሮ እስከ 2016 ዓ/ም ድረስ ከፍተኛ ውጤት የተመዘገበ መሆኑን ክቡር ሚኒስትር ዴኤታ በስፋት በንፅፅር አስረድተዋል።

ክቡር ሚኒስትር ዴኤታ አያይዘውም ሀገራችን የኮቪድ እና የሀገር ውስጥ ችግሮችን ተቋቁማ ከሰሃራ በታች ካሉ ሀገሮች በኢኮኖሚ አፈጻጸም ከፍተኛ ውጤት ማስገኘት መቻሏንም አብራርተዋል።

Share this Post