በክቡር ሚኒስትሩ የተመራ ቡድን ብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ፕሮግራምን ጎበኙ፡
በክቡር ሚኒስትሩ የተመራ ቡድን ብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ፕሮግራምን ጎበኙ፡
መጋቢት 04/2016 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃ ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ የተመራ ቡድን የፋይዳ ብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ፕሮግራምን ጎበኙ፡፡
በጉኝቱ በፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ፕሮግራም አጠቃቀም፣ አወጣጥ ፣ጠቀሜታና ደህንነት ዙሪያ ያሉትን ሂደቶች ጎብኝተዋል፡፡ በጉብኝቱ ወቅት በተለይ እንደ ውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር ይህን ፕሮግራም ወደ ራሳችን በመውሰድ በጀመርናቸው ዲጂታላይዝድ የማደረግ ስራዎች ላይ አስተዋጾ ስለሚኖረው ውል መግባት ድረስ በመሄድ አብረን የምንሰራበትን ሁኔታ እንደሚፈጠር በጉብኝቱ ወቅት ተገልጿል፡፡
የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮዳሄ ዘሚካል ዲጂታል መታወቂያ ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር የተያያዙ ችግሮችን በማቃለል ለኢኮኖሚያዊ እድገት መሰረት የሚጥል በመሆኑ ሁሉም ማህበረሰብ ቋሚ አድራሻ ባይኖረውም አገልግሎቱን መጠቀም እንደሚችል ገልጸዋል፡፡