የውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር በቦሌ ክፍለ ከተማ ለሚገኙ አቅመ ደካሞች የህረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ አደረገ
የውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር በቦሌ ክፍለ ከተማ ለሚገኙ አቅመ ደካሞች የህረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ አደረገ
መጋቢት 4/2016 (ውኢሚ) የውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር በቦሌ ክፍለ ከተማ ለሚገኙ አቅመ ደካሞችና የአካል ጉዳተኞች የህረተሰብ ክፍሎች ከ67ሺ ብር በላይ ወጪ በማደረግ የአልባሳት ድጋፍ አደረገ፡፡
ድጋፉን በአካል በመገኘት ያበረከቱት የውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ ሲሆኑ የውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር በበጎ አድራጎት ተግባራት የተለያዩ ስራዎችን በአዲስ አበባ ብቻም ሳይሆን ክልል ድረስ በመውረድ የቁሳቁስ ድጋፎችን ፤የቤት እድሳትን ጨምሮ የተለያዩ የበጎ አድራጎት ተግባራትን እያደረገይገኛል፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በክፍለ ከተማው የሚገኙ 30 ቤተሰቦችን በቋሚነት እየደገፈ የሚገኝ ሲሆን የዛሬው ድጋፍም የዚሁ አንድ አካል ነው፡፡
በቦሌ ክፍለ ከተማ የሴቶች፣ ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳዮች ጽ/ቤት ሀላፊ የሆኑት ወ/ሪት ትእግስት ለገሰ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገ መሆኑን ጠቀወሰው ቤት ከማደስ ለበአል ማእድ ከማጋራት በተጨማሪ በቋሚነት 30 ቤተሰቦችን ይዞ ድጋፍ እያረገ በመሆኑ በተረጂዎች ስም አመስግነዋል፡፡