ለመጠጥ ውሃ አቅርቦት ዘርፍ የተሰጠው ትኩረት አበረታች መሆኑ ተጠቆመ።

ለመጠጥ ውሃ አቅርቦት ዘርፍ የተሰጠው ትኩረት አበረታች መሆኑ ተጠቆመ።

የካቲት 29/2016 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ለመጠጥ ውሃ አቅርቦት ዘርፍ የተሰጠው ትኩረት አበረታች መሆኑ ተጠቆመ።

የከተማ የውሃ አቅርቦት ጥናትና ዲዛይን መመዘኛና መለኪያ ጋይድላይን ላይ በተደረገው የውይይት መድረክ ላይ ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ሱፐርቪዥን ኮርፖሬሽን የመጡት ከፍተኛ የውሃ መሀንዲስ ወ/ሮ ሙሉ ባምቦሬ በሰጡት አስተያየት ተቋሙ ለመጠጥ ውሃው ዘርፍ የተሰጠው ትኩረት የሚበረታታ መሆኑን ፤ ከከተሞች መስፋፋት ጋር ተያይዞ ለውሃ አቅርቦት የሚያገለግሉ ግብዓቶች የዋጋ ንረትን ታሳቢ ያደረገ ጋይድላይን በመሆኑ በዶክመንቱ ላይ ከባለድርሻዎች ጋር ለመወያየት የተደረገውን ጥረት አድንቀዋል።

ወ/ሮ ሙሉ አክለውም ኮንሰልታንትና ኮንትራክተሮችን ከመምረጥ ጋር ተያይዞ ከግለሰብ የፀዳ ሆኖ መሰራቱ በተቋሙ የውሃ አቅርቦት ሽፋንን ያሻሽላል ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል።

በጋምቤላ ክልል የውሃና ኢነርጂ ቢሮ በCR-WaSH ፕሮጀክት ላይ የውሃ መሀንዲስ የሆኑት አቶ አሸናፊ አየለ በበኩላቸው በተሰጠው አስተያየት መሰረት በሀገሪቱ ለከተማ መጠጥ ውሃ የሚሰሩ የጥናትና ዲዛይን ዶክመንቶች ይህንን የዲዛይን መስፈርት እና መመሪያ ተከትለው ከተሰሩ ዘላቂ የውሃ አቅርቦትን ለማረጋገጥ የሚያስችል ሲሆን፤ የዜጎችንም የውሃ ተጠቃሚነት ቀጣይነት ያለው እንዲሆን ያስችላል ብለዋል።

በተጨማሪ ከዚህ ቀደም የነበረውን መመሪያ ከመጠቀም ይልቅ ወቅታዊ የከተማ መጠጥ ውሃ ዲዛይን መስፈርትና መመሪያ መዘጋጀቱን አድንቀዋል።

አቶ አሸናፊ አክለውም ተቋሙ በጋምቤላ ከተማ በCR-WaSH የሚሰሩ የውሃ ተቋማት ግንባታ ስራዎች ላይ ፈንድ ከማፈላለግ ጀምሮ የነበረውን ክትትልና ድጋፍ ተጠናክሮ ቢቀጥል ብለዋል።

Share this Post