በክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ የተመራ ቡድን በግምቢቹ ወረዳ የተለያዩ የመጠጥ ውሃና ኢነርጂ ፕሮጀክቶች የመስክ ምልከታ ተካሂዷል።

በክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ የተመራ ቡድን በግምቢቹ ወረዳ የተለያዩ የመጠጥ ውሃና ኢነርጂ ፕሮጀክቶች የመስክ ምልከታ ተካሂዷል።

ጥር /2016 ዓ/ም በክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ የተመራ በሕ/ተ/ም የውሃ፣ መስኖ፣ ቆላማ አካባቢዎችና አከባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት፤ የመሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት እና በጨፌ ኦሮሚያ የመሰረተልማት አስባባሪ የተካቱበት በግምቢቹ ወረዳ የተለያዩ የመጠጥ ውሃና ኢነርጂ ፕሮጀክቶች የስራ እንቅስቃሴዎች የመስክ ምልከታ አካሂደዋል።

የመስክ ጉብኝቱን የመሩት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ ዘንድሮ በተለያዩ ክልሎች ተመሳሳይ የመስክ ምልከታ መካሄዱን አስታውሰው፤ የጉብኝቱ ዋና አላማም በአፈፃፀም ሂደት ያጋጠሙትን ችግሮች በመለየት የመፍትሄ አቅጣጫ ማስቀመጥ እና ክልሎችም ለመደገፍ ታሳቢ ያደረገው መሆኑን ገለፀዋል።

በዚህ ፕሮግራም ከአቅማችን በላይ የሆኑ ጉዳዮችን የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አካላት ችግሮቹን ተረድቶ ድጋፍ እንዲያደርጉ በጋራ የመስክ ምልከታ እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል።

ክቡር ሚኒስትሩ አያይዘውም በውሃና ኢነርጂ ሥራዎች እጂግ ውጤታማ ሥራዎች ማየታቸውን ገልፀው፤ በተለይም በትምህርት እና በጤና ተቋማት ላይ ከሶላር ኃይል የኢነርጂ አቅርቦት ጋር በተያያዘ የተሰሩ ስራዎች አበረታች መሆናቸውን ገልፀዋል።

የሶላር ኢነርጂ የማቅረብ ስራውም ዘላቂ አገልግሎት መስጠት እንዲያስችል ከወረዳ ጋር በመቀናጀት ወጣቶችን በማደራጀት በባለቤትነት እንዲያስተዳድሩ ማድረግ ይጠበቅብናል ብለዋል።

በመጠጥ ውሃ አቅርቦት በወርልድ ቪዥን እና በካቶሊክ የግብረሰናይ ድርጀቶች የእተሰሩ ያሉ ሥራዎች መልካም ቢሆኑም፤ መስተካከል የሚገባቸው ክፍተቶች መኖራቸውንም በአፅንኦት ተናግረዋል።

ክቡር ሚኒስትሩ አክለውም የታዩት ክፍተቶች ለመቅረፍ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርግ ገልፀዋል።

በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የሚኒስትሩ አማካሪ አቶ አበራ እንዳሻው በበኩሉ በውሃና ኢነርጂ ዘርፍ እየተሰሩ ያሉ ሥራዎች የመስክ ምልከታ ቅኝት በማድረግ ግብዓት ለማሰባሰብ እና ጠንካራ ጎኖችን በማስፋፋት ከደካማ አፈጻጸሞች ትምህርት ወስደው የእርምት እርምጃ ለመውሰድ ጉብኝቱ ጠቀሜታው የጎላ ነው ብለዋል።

በመስክ ምልከታ ቆይታው የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በሞጆ ከተማ ያስገነባቸውን የአቅመደካማ ነዋሪዎች ቤት ርክክብና የአዳማ ከተማ መጠጥ ውሃ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ግምባታ ጉብኝት ይደረጋል።

Share this Post