በክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሡልጣን ወሊ በተመራ ቡድን በፀሐይ ኃይል መስኖን የሚያለማ የሶላር ቴክኖሎጂ ጉብኝት ተደረገ፡፡
በኢነርጂ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ድኤታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሡልጣን ወሊ በተመራ ቡድን በፀሐይ ኃይል መስኖን የሚያለማ የሶላር ቴክኖሎጂ ጉብኝት ተደረገ፡፡
የካቲት 2016 ዓ/ም (ው.ኢ.ሚ) በኢነርጂ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሡልጣን ወሊ የተመራ ቡድን በፀሐይ ኃይል መስኖን የሚያለማ የሶላር ቴክኖሎጂ ጉብኝት ተደረገ፡፡
በጉብኝቱ ወቅት ማብራሪያ የሰጡት ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሡልጣን ወሊ በኢትዮጵያ ከ8 ሚሊዮን ሄክታር በላይ በመስኖ የሚለማ መሬት መኖሩን ገለፀው፤ 800 ሽህ ሄክታር መሬት በፓምፕ የሚለማ ነው ብለዋል። የነዳጅ ፓፕም መጠቀም ከፍተኛ ወጪ የሚያስከትል በመሆኑ፤ የሶላር ኃይል መጠቀም የማይተካ አማራጭ መሆኑ አነስተዋል።
ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው አክለውም ከወጪ ተፅዕኖ በሻገር የነዳጅ አቅርቦቱ ፈታኝ በመሆኑ በነዳጅ የሚሰሩ የመስኖ ፓምፖችን በሶላር መስኖ ፓምፖች ለመተካት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ከኔዘርላንድስ መንግስት የልማት ድርጅት፣ ከፌዴራል፣ ከክልል ውሃ ቢሮዎች እና የግብርና ሴክተሮች ጋር በመቀናጀት ሥራ መጀመሩን ሚኒስትር ድኤታው አስረድተዋል።
እስከ 2015 ዓም ግማሽ ሚሊዮን የዲዝል ጀኔሬተሮች በመንግሥትና በግል ባለሀብቶች ተገዝተው ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ መሆኑን ገልጸው፤ ጥቅም ላይ መዋላቸው በአከባቢ ላይ ከፍተኛ የአየር ብክለት ስለሚያስከትል የዲዝል ጄኔሬተሮችን በመቀነስ የሶላር ቴክኖሎጂን በስፋት መጠቀም ይገባል ብለዋል።
በሲዳማ ከክልል ሸበዲኖ ወረዳ የሶላር መስኖ ፀሐይና በደመና ጊዜ በትንሹ በሰዓት ከ3.5 ኪሎ ዋት ኃይል እንደሚያመነጭ ጠቁመው በአሁኑ ወቅት በሲዳማ፣ በኦሮሚያ፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ እና በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስታት መስኖን የሚያለማ የፀሐይ ኃይል መጀመሩን ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ገልፀዋል፡፡
የሲዳማ ክልል ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ከበደ ጋኖሌ በበኩላቸው በክልሉ እስከ አሁን መስኖን በዲዝል ፓምፕ እያለሙ እንደሆነ ገልፀው፤ በሸበዲኖ ወረዳ የተተገበረው በሶላር ኃይል የሚሠራ የታዳሽ ኢነርጂ የመጀመሪያው የሙከራ ፕሮጀክት ነው ብለዋል።
በሶላር የሚሰሩ ቴክኖሎጂዎች ከዲዝል ጀኔሬተሮች ጋር ሲነፃፀሩ፤ ብቀታቸው በእጥፍ እንደሚበልጡ የገለፁት ኃላፊው፤ አርሶአደሩ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በስፋት እንዲጠቀሙ ማመቻቸት ይጠበቅብናል ብለዋል።
የሸበዲኖ ወረዳ በፀሐይ የሚሠራ የሶላር ኢነርጂ ተጠቃሚ ማህበር ስብሳቢ አቶ ሳሙኤል ወድሶ የሶላር ቴክኖሎጂ ከተሠራላቸው ጀምሮ በቀን ከ8 ሰዓት በላይ የተለያዩ አትክልቶችን ውሃ እንደሚያጠጡ ገልፀው፤ የሶላር ቴክኖሎጂን ከመግኘታቸው በፊት ለጄኔሬተር ነዳጅ የሚወጣው ወጪ በተጨማሪ ሙሉ ቀን መጠቀም እንዳልቻሉ ተናግረዋል።
በኔዘርላንድ የልማት ድርጅት (SNV) የኢነርጂ ዘርፍ ኃላፊው ወ/ሮ ህይወቴ ተሾመ በበኩላቸው ፕሮጀክቱ ዘላቂ ኢነርጂ ለአነስተኛ አርሶአደር በሚል እየተሰራ ሲሆን በኢትዮጵያ፣ በኬንያ እና በዩጋንዳ በግብርና እና በእንስሳት ውጤቶች ላይ ትኩረት ተሰጥቶት ንፁህ ኢነርጂ አጠቃቀም ማበረታታት የሚገበር መሆኑንአንስተዋል።
የኢነርጂ ዘርፍ ኃላፊዋ አያይዘውም ንፁህ ኢነርጂ አጠቃቀም ዘለቄታዊ እንዲሆን ቴክኖሎጂውን ማበረታታት ብቻ ሳይሆን መንግስት የግል ዘርፉ ጋር በመተባበር የገበያ ትስስር መፍጠር ሲሆን በዚህ የሙከራ ፕሮጀክት አርሶ አደሩ የፕሮጀክቱን ወጪ 30% እና ድርጅታቸው 70% እየሸፈነ መሆኑን ገልፀዋል።