ክቡር ሚኒስትሩ በዓለም መንግሥታት ጉባኤ ላይ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ፡፡

ክቡር ሚኒስትሩ በዓለም መንግሥታት ጉባኤ ላይ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ፡፡

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ በተባበሩት ዐረብ ኢምሬትስ፤ በዱባይ እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም መንግስታት ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ።

መንግስታት፣ አለማቀፍ ድርጅቶች፣ የግሉ ዘርፍ አመራሮች እና ከአለም ዙሪያ የተሰባሰቡ ሌሎች አካላት በአለምአቀፍ ትብብር መስክና ለመጪ ጊዜ ተግዳሮቶች ፈጠራ አዘል መፍትሄዎች ላይ እ.ኤ.አ ከፌብሪዋሪ 12/2024 ጀምሮ እየመከረ በሚገኘው ጉባዔ ላይ እየተሳተፉ ይገኛል፡፡

በጉባኤው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒሰቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር በለጠ ሞላ፤ የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ኢ/ር አይሻ መሃመድ፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደደር ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

Share this Post