በኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ የከርሰ ምድርውሃ ፕሮጀክት በአካባቢያዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ማስፈጸመያ መመሪያ ላይ ስልጠና እየሰጠ ነው፡፡

በኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ የከርሰ ምድርውሃ ፕሮጀክት በአካባቢያዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ማስፈጸመያ መመሪያ ላይ ስልጠና እየሰጠ ነው፡፡

የካቲት /2016 ዓ.ም የአካባቢ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ማስፈጸሚያ የህግ ማዕቀፍ ዙሪያ ለባለድርሻ አካላት ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡

መርሀ ግብሩን በንግግር ያስጀመሩት በውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስቴር ዲኤታ ክቡር አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ በኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ የከርሰ ምድር ውሃ ፕሮጀክት በአምስት የቀንዱ አገራት ኢትዮጵያ፣ ኬኒያ፣ ሶማሊያ፣ ጂቡቲና ደቡብ ሱዳን በጠረፋማ አካባቢዎች ለሚኖሩ የተለያዩ የልማት ስራዎችን ለመደገፍ የተቀረጸ ፕሮጀክት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው በማያያዝ አምስቱ አገራት በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ችግሮች በተደጋጋሚ የሚጠቁ ሲሆኑ በነዚህ አካባቢዎች ካሉ የልማት ችግሮች የመጠጥ ውሃ እና መስኖ ልማት ዋነኛ ችግሮች በመሆናቸው ይህን ችግር ለመፍታት በአለም ባንክ የገንዘብ ድጋፍ ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት አካባቢያዊ እና ማህበራዊ የልማት አገልገሎቶች ላይ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል ብለዋል፡፡

ክቡር አምባሳደር አስፋው በመጨረሻም የዚህ ስልጠና አላማ ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ ለማድረግ በአካባቢያዊና ማህበራዊ ጉዳዮች የወጡትን ማስፈጸሚያ መመሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ለማስተዋወቅ መሆኑን በመጠቆም፤ ይህን ስልጠና በአግባቡ ስራ ላይ ማዋል እጅግ አስፈጊ መሆኑን ጠቁመው በተለይ በወረዳ ደረጃ ያሉ ባለድርሻ አካላት ይበልጥ ትኩረት በመስጠት አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል በማለት መርሀ ግብሩን አስጀምረዋል፡፡

በኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ የከርሰ ምድር ውሀ ፕሮጀክት 20 የመጠጥ ውሀ እና የመስኖ ፕሮጀክቶች የተጀመሩ ሲሆን ፕሮጀክቶቹ በሚተገበሩባቸው አካባቢዎች ላሉ የክልል ፣የወረዳ፣ ከፌደራል ለመጡ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር እንዲሁም የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስቴር ባለሙያዎች እና ለሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ስልጠናው እየተሰጠ ነው፡፡

ስልጠናው ለአምስት ተከታታይ ቀናት የሚቀጥል ሲሆን ሁለተኛ ዙር ስልጠናም በሀዋሳ እንደሚሠጥ ከአስተባባሪዎች ማወቅ ችለናል፡፡

Share this Post