የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከፓኪስታን ከፍተኛ የመንግስት ልኡካን ጋር በውሃና ኢነርጂ ዙሪያ ውይይት አደረገ፡፡

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከፓኪስታን ከፍተኛ የመንግስት ልኡካን ጋር በውሃና ኢነርጂ ዙሪያ ውይይት አደረገ፡፡ ህዳር 12/2016 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከፓኪስታን ከፍተኛ የመንግስት ልኡካን ጋር በውሃና ኢነርጂ ዙሪያ ተወያዩ፡፡ ውይይቱን በእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ያስጀመሩት የክቡር ሚኒስትር ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ማሙሻ ሀይሉ የተቋሙን አደረጃጀት፣ ተግባርና ኃላፊነት ካስተዋወቁ በኋላ መድረኩን ለውይይት ክፍት አድርገዋል፡፡ ልኡካን ቡድኑ ኢትዮጵያ በውሃ፣ በኢነርጂና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ያላትን ልምድ ለመካፈል መምጣታቸውን ገልጸው፤ ሚኒስቴር መ/ቤቱ ኢነርጂን ከማመንጨት የሜመንጨት ሂደት ላይ፣ የውሃ ፖሊሲ እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ፣ ታዳሽ ኢነርጂን በተመለከተ ያለው ተሞክሮን በተመለከተና የዋሃና ኢነርጂ ዘርፎች የአደረጃጀትና የሚመራበት ሂደት ላይ ጥያቄዎችን በማንሳት ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡ በተነሱት ጥያቄዎች ላይ በየዘርፉ የስራ ሀላፊዎች ሰፊ ምላሽ የተሰጠ ሲሆን፤ የልኡክ ቡድኑ እንደ ሀገር እየተተገበረ የሚገኘው የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር ላይ ያለውን ተሞክሮም እንዳስደነቃችው አስተያየት ሰጥተዋል፡፡

Share this Post