የህዝብ ተወካዮች ም/ቤትና የፌዴሬሽን ም/ቤቶች የጋራ ጉባኤ ላይ መክፈቻ ንግግር

የህዝብ ተወካዮች ም/ቤትና የፌዴሬሽን ም/ቤቶች የጋራ ጉባኤ ላይ በመክፈቻ ንግግር ክብርት ሳህለወርቅ ዘውዴ ዘርፉን በተመለከተ የጠቀሷቸው ጉዳዮች፡- ~ ባለፈው አመት የውሃ አቅርቦትን ለማሻሻል በተደጋጋሚ የውሃ ችግር በሚያጋጥሙ ቦታዎች የውሃ አቅርቦት እንዲያገኙ ተደርጓል፤ ~ የጎርፍ ስጋት ያለባቸውን ቦታዎች የአደጋ ተጋላጭነትን ለመቀነስ አበረታች እንቅስቃሴዎች ተከናውነዋል፤ ~ የህዳሴ ግድብን በተመለከተ የሚደረጉ ድርድሮች ሀገራችን በተፈጥሮ ሀብቷ የመልማት መብት እንዲሁም የተፋሰሱን ሀገራት የማልማት ዕድል በማይነፍግ መልኩ ይከናወናል፤እኩል ተጠቃሚነትን መሰረት አድርጎ በሰላማዊ መንገድ ድርድሮችን ለመጨረስ ይሰራል፤

Share this Post