የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላም ሰራዊት አባላት የውሃና ኢነርጂ አውደርእይን ጎበኙ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላም ሰራዊት አባላት የውሃና ኢነርጂ አውደርእይን ጎበኙ። መስከረም 10/2016 ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) "የውሃ ሀብታችን ለብልፅግናችን!" በሚል መርህ የተዘጋጀውንና በዛሬው እለት የሚጠናቀቀውን የውሃና ኢነርጂ አውደርእይን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላም ሰራዊት አባላት ጎበኙ። ከጉብኝቱ በኋላ ያነጋገርናቸው የሰራዊቱ አባላት እንዳሉት የሀገራችን የውሃ ሀብት ያለበትን ደረጃ እንድናውቅ የተደረገበት መንገድ ወደፊትም በሌሎች ተቋማት ተጠናክሮ ቢቀጥል ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል። አያይዘውም የሁላችንም አሻራ ያረፈበት የህዳሴ ግድባችን ያለበትን አሁናዊ ደረጃ በቴክኖሎጂ ታግዞ ያየንበት መንገድ ከቦታው ሄደን መጎብኘት ላልቻልን ኢትዮጵያዊያን ትልቅ ዕድል የፈጠፈ ነው ብለዋ።

Share this Post