ቴክኖሎጂውን በተግባር ያየንበት ኤግዚቢሽን ነው። የአራዳ ክ/ከተማ ጎብኚዎች

ቴክኖሎጂውን በተግባር ያየንበት ኤግዚቢሽን ነው። የአራዳ ክ/ከተማ ጎብኚዎች የአራዳ ክ/ከተማ የስራ ዕድል ፈጠራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ፅ/ቤት አመራሮች፣ ሠራተኞችና በክፍለ ከተማው በተለያየ ዘርፍ ላይ የተደራጁ የህብረት ስራ ማህበራት የውሃና ኢነርጂ ኤግዚቢሽንን ጎበኙ። "ውሃ ሃብታችን ለብልፅግናችን!" በሚል መርህ የተዘጋጀውንና ሊጠናቀቅ ቀናት ብቻ የቀረውን ሀገራዊ ኤግዚቢሽን ሲጎበኙ በሰጡት አስተያየት ኤግዚቢሽኑ በስራ ዕድል ፈጠራ የተደራጁ ማህበራት ላይ ትልቅ የስራ መነሳሳት የፈጠረ ነው ብለዋል። ጎብኚዎቹ በሰጡት አስተያየት ቴክኖሎጂው በምን ያህል ፍጥነት ወደፊት እየተጓዘ እንደሚገኝ በተግባር ያሳየን ኤግዚቢሽን ሆኖ ነው ያገኘነው ብለዋል።

Share this Post