ከተጀመረ ወደ አንድ ወር የተጠጋው አውደርእይ በበርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች እየተጎበኘ ነው፡፡

የውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር በሳይንስ ሙዚየም ያዘጋጀው ከተጀመረ ወደ አንድ ወር የተጠጋው ሀገር አቀፍ አውደርእይ በበርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች እየተጎበኘ ነው፡፡ መስከረም 05/2016ዓም(ው.ኢ.ሚ) በዛሬው እለትም ከተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢ እና የሸገር ሲቲ ነዋሪዎች ጎብኝተውታል ከነዚህም የአዲስአበባ ደንብ ማስከበር አባላት፣ የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት ሰራተኞች አንቀሳቃሾች፣ የንፋስ ስልክ ለፍቶ ክፍለ ከተማ ሴቶች ና ህጻናት ሰራተኞች፣ የሸገር ሲቲ የስራ ፈጠራና ክህሎት አመራር ፣ ሰራተኞች እና ነዋሪዎች እንዲሁም የሰበታ ከተማ ነዋሪዎች የሳይንስ ሙዚየሙን ጎብኝተዋል ፡፡ የውሀና ኢነርጅ ሚኒስቴር "የውሀ ሀብታችን ለብልጽግናችን" በሚል በሳይንስ ሙዚየም ለእይታ ከቀረበ ጀምሮ አምባሳደሮች፣ ሚንስትሮች፣ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የመጡ ሰዎችና የውጪ ዜጎች፣ የሚዲያ አካላት የጎበኙት ሲሆን ሁሉም ጎብኝዎች የውሃና ኢነርጂ በውሀ ሀብት አስተዳደር፣ በመጠጥ ውሃ ሽፋን በአማራጭ ኢነርጂ የደረሰበትን የቴክኖሎጂ እና ከፍታ ያዮበት መሆኑ በተደጋጋሚ ተገልጿል፡፡ በዛሬው እለትም በሽዎች የሚቆጠሩ ጎብኝዎች ተመሳሳይ ሀሳባቸውን አጋርተውናል፡፡ በመጨረሻም አውደርእዩ ሊጠናቀቅ ጥቂት ቀናት ብቻ የቀረው በመሆኑ እንድትጎበኙ ጥሪ እናስተላልፋለን፡፡

Share this Post