የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አመራሮች እና የማኔጅመንት አባላት አገርአቀፍ የውሃና ኢነርጂ ኤግዚቢሽንን ጎበኙ።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አመራሮች እና የማኔጅመንት አባላት አገርአቀፍ የውሃና ኢነርጂ ኤግዚቢሽንን ጎበኙ። መስከረም 3/2016 ዓ/ም የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አመራሮች እና የማኔጅመንት አባላት በሳይንስ ሙዚየም በመገኘት አገርአቀፍ የውሃና ኢነርጂ ኤግዚቢሽን ጎበኙ። የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጌትነት ታደሰ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር እየተሰሩ ያሉ ፕሮጀክቶችና በዘርፉ እየተተገበሩ ያሉ ቴክኖሎጂዎች እንደሀገር ከፍተኛ ጠቀሜታ እዳላቸው ገልጸዋል። ሀገር የሚፀናው ሁሉም ተቋማት በሚያደርጉት ደረጃውን የጠበቀ ሥራ ነው ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚው የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ባለሙያዎች እና የተጠሪ ተቋማት የውሀ ሀብታችንን ለማጥናትና ለመጠበቅ እያደረጉት ያለውን አስተዋፅኦ የሚያሳይ ገላጭ ኤግዚቢሽን ነው ብለዋል።

Share this Post