የውሃ ወለድ በሽታዎችን በቅንጅት መከላከል እንደሚገባ ክቡር አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ ገለፁ።

የውሃ ወለድ በሽታዎችን በቅንጅት መከላከል እንደሚገባ ክቡር አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ ገለፁ። መስከረም /2016 ዓ/ም አገርአቀፍ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ኤግዚቢሽን የጤና ሚኒስቴር አመራሮች እና የማኔጅመንት አባላት በሳይንስ ሙዝየም በመገኘት በጎበኙበት ወቅት የውሃ ወለድ በሽታዎችን በቅንጅት መከላከል እንደሚገባ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ ገለፁ። ከ60 እስከ 80 በመቶ ተላላፊ በሽታዎች በውሃ ወለድ የሚከሰቱ በሽታዎች መሆኑን ክቡር አምባሳደሩ ገልፀው፤ በመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዙሪያ ከጤና ሚኒስቴር ጋር የውሃ ወለድ በሽታዎችን በቅንጅት ለመከላከል እየተሰራ ነው ብለዋል። የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ሽፋን በከተማ እና በገጠር በአማካይ ከ60 - 70 በመቶ መድረሱን ገልፀው የሳኒቴሽን አገልግሎት በ2030 የዘላቂ የልማት ግቦችን እውን ለማድረግ የባለድርሻ አካላት ርብርብ እንደሚያስፈልግ ክቡር አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ በመግለጽ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

Share this Post