የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ሀላፊዎችና አባላት የውሃና ኢነርጂ አውደርዕይን ጎበኙ።

ጳጉሜ 4- የአምራችነት ቀን ኢትዮጵያ ከሸማችነት ወደ አምራችነት - በዚህ እለት በውሃና ኢነርጂ ዘርፍ ሀገራችን የደረሰችበትን የቴክኖሎጅ ደረጃ ያየንበት ሲሉ የአዲስ አበባ ደንብ ማሰከበር ጽ/ቤት ኃላፊዎች ስለ አውደርዕዩ ተናገሩ ። ጳጉሜ 4/2015ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ሀላፊዎችና አባላት የውሃና ኢነርጂ አውደርዕይን ጎበኙ። አቶ ተስፋሁን አሉላ የልደታ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ ሀገራችን በውሃው ዘርፍ ደመናን በማበልጸግ፣ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ስርአቱን ለማሻሻል እየተሰራ ያለው እንዲሁም የህዳሴ ግድባችን አሁናዊ ሁኔታ አገራችን በዘርፉ የደረሠችበትን ደረጃ ያሳየ አውደ ርዕይ ብለውታል። አክለውም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ይህንን የመሠለ ስራ እንድንጎበኝ ማድረጉ ስራውን ከማስተዋወቅ ባለፈ እኛ የምንማርባቸው እና ጠቃሚ የሆኑ ቴክኖሎጅዎችን እንድንተዋወቅ አድርጓል ብለዋል። በተለይም የህዳሴ ግድባችን በአካል ያየነው ያክል ሆኖ የቀረበበት መንገድ እጅግ የረቀቀ ቴክኖሎጅ ላይ መድረሳችን ያሳያልም ብለዋል። ሻለቃ ዋጋሪ አቶምሳ የወረዳ 1 ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ በበኩላቸው በአውደርዕዩ እጅግ በጣም እንደተደነቁ ገልጸው በተለይም የሀገራችን የውሃ ሀብት በማልማት በአግባቡ ለመጠቀም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እየሰራ ያለው ስራ እና ያሉ ቴክኖሎጅዎች የሀገራችን ብልጽግና ለማረጋገጥ ወሳኝ መሆናቸውን አውደ ርዕዩ ያስገነዝባል ብለዋል። በእለቱ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ ለጎብኝዎቹ ለእይታ የቀረቡትን የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ስራዎችን እየተዝናኑ እንዲጎበኙ እና በርካታ ጠቃሚ ቴክኖሎጅዎችን እንዲተዋወቁ ቅድመ እውቅና እንዲኖራቸው አድርገዋል።

Share this Post