የሳይንስ ሙዚየሙ የተቋማት ስራ ጎልቶ እንዲወጣ መንገድ ከፍቷል ተባለ፡፡

የሳይንስ ሙዚየሙ የተቋማት ስራ ጎልቶ እንዲወጣ መንገድ ከፍቷል ተባለ፡፡ ጳጉሜ 03/2015 ዓ.ም(ው.ኢ.ሚ) የኦሮሚያ ውሀና ኢነርጂ ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች በሳይንስ ሙዚየም የተዘጋጀውን ሀገር አቀፍ አውደርእይ ጎበኙ፡፡ አውደርእዩ ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ውሀና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ ኢ/ር ሚሊዮን በቀለ ይህ የሳይንስ ሙዚየም መገንባቱ ተቋማት ስራዎቻቸው ጎልተው እንዲወጡ፤ በተለይ እንደ ውሀና ኢነርጂ ያሉ በቴክኖሎጂ የተደገፉ በርካታ ስራዎችን እየተሰሩ መሆኑ ህብረተሰቡ እንዲያውቅና የልማቱ አጋዥ እንዲሆን ትልቅ የሆነ አበርክቶ አለው ብለዋል፡፡ ኢ/ር ሚሊዮን አክለውም የውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከውሀ አፈጣጠር እስከ አጠቃቀም ያለውን ሂደት እና ውጣ ውረድ በትክክል ያሳየ በመሆኑ ህብረተሰቡ የውሃን ከየት ወዴት የሚለውን እንዲረዳ ያደረገ ነው በማለት ገልጸዋል፡፡ ኃላፊዋ አያይዘውም የታዳሽ ሀይል እና ኤሌክትሪክ ተጠቃሚ እና አገልግሎት ሰጪ መካከል ቅርርብ የሚፈጥሩ ተግባራት አጉልቶ ያሰየ በመሆኑ ሌሎች ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችም ይህንን አውደ ርእይ ተመልክተው ቢጠቀሙበት ውጤታማ ሊሆኑ እንደሚችሉ መናገር እወዳለሁ ብለዋል፡፡

Share this Post