የውሃና ኢነርጂ ስራዎች ሳይንሳዊ ሆነው እንዴት ተሰንደው እንደቀረቡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትምህርት የሚቀስምበት አውደ ርዕይ ነው፡፡

የውሃና ኢነርጂ ስራዎች ሳይንሳዊ ሆነው እንዴት ተሰንደው እንደቀረቡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትምህርት የሚቀስምበት አውደ ርዕይ ነው፡፡------ ክቡር አምባሳደር መለሰ አለም ጷጉሜ 3/2015 ዓ.ም(ው.ኢ.ሚ) በክቡር አምባሳደር መለሰ አለም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ የተመራ አመራሮችና ባለሙያዎች የውሃና ኢነርጂ አውደ ርዕይን ጎበኙ። ክቡር ቃልአቀባዩ በነበራቸው ጉብኝት በሰጡት አስተያየት የበርካታ ሴክተሮች ትልቅ ችግር የሆነው ታሪካዊ ክንውኖችን ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ በሚገባ ሰንዶ ለትውልድ ማስተላለፍ መሆኑን ጠቁመው፤ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሄደባቸው መረጃን በማዘመን የመሰነድ ስትራቴጅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም ሆነ ሌሎች የመንግስት ተቋማት ልምድ ሊወስዱበት የሚገባ አውደ ርዕይ ነው ሲሉ ገልጸውታል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ጋር በውሃ ዲፕሎማሲ፣ በድንበር ተሻጋሪ የውሃ ሀብቶችና በህዳሴው ግድብ ዙሪያ በጋራ የሚሰሯቸው ተግባራት እንዳሉ የጠቀሱት ክቡር ቃል አቀባዩ፤ በጉብኝቱ በርካታ ነገሮችን መማራቸውንና በቀጣይ በጋራ በሚሰሩ ስራዎች ዙሪያ መነጋገር እንደሚገባ ትምህርት የወሰድንበት አውደርዕይ ነው ብለውታል። በአጠቃላይ ጠቃሚ እና ታሪካዊ መረጃዎች በሚገባ ሳይንሳዊ ሆነው የተሰነዱበት እንዲሁም ለትውልድ የሚተላለፍበት ይበል የሚያሰኝ አውደርዕይ ሲሉ በጉብኝታቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል።

Share this Post