የኢነርጂ ልማት ለኢንዱስትሪ መስፋፋት ወሳኝ ነው ተባለ፡፡

የኢነርጂ ልማት ለኢንዱስትሪ መስፋፋት ወሳኝ ነው ተባለ፡፡ የውሀና ኢነርጅ ሚኒስቴር በሳይንስ ሙዚየም ያዘጋጀውን አገር አቀፍ አውደርእይ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች ጎብኝተዋል፡፡ ጳጉሜ03/2015ዓ.ም(ው.ኢ.ሚ)የኢንደስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ታረቀኝ ቡልልታ በጉብኝታቸው ወቅት ሀገራችን ላይ ብዙ ያልተጠቀምንባቸው ሀብቶች እንዳላት እና አሁን ላይ የውሀ ሀብታችንን በአግባቡ ተጠቅመን መበልጸግ የምንችልበትን የእድገት ጎዳና ላይ መሆናችችን ያየንበት አውደርእይ ነው ብለዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ የተለያዩ የኢነርጂ አማራጮችን በመጠቀም የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥና የኢንዱስትሪዎችን ምርታማነት መጨመር እንደሚቻል ገልጸው፤ በተለይ የንፋስ ሀይል ፣ የባዮ ጋዝ እና ሶላር ሀይል አጠቃቀምን በማሻሻል ያለንን እምቅ ሀብት ማሰደግ የምንችልበትን ሁኔታ እንዳለ መረዳታቸውን አንስተዋል፡፡ ክቡር ሚንስትር ዲኤታው በማከል የኢንዱስትሪም ሆነ ሌሎች እንቅስቃሴዎች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ካለ ውሀና ኢነርጂ አንድ እርምጃ መንቀሳቀስ ስለማይችሉ፤ የውሀ ሀብታችንን በአግባቡና በቁጠባ በመጠቀም አማራጭ ኢነርጂ ላይ ትኩረት በማድረግ የነዳጅ ፍጆታን በመቀነስ የውጭ ምንዛሬን ማስቀረት እንደሚቻል እና የውሀና ኢነርጂ ያለበትን የቴክኖሎጂ ከፍታ የተገነዘብንበት አውደ ርእይ ነው በማለት ገልጸዋል፡፡

Share this Post