የቀድሞ የውሃ ልማት ሚኒስትር የነበሩት ክቡር አምባሳደር ሽፈራው ጃርሶ የውሃና ኢነርጂ አውደርዕን ጎበኙ።

የቀድሞ የውሃ ልማት ሚኒስትር የነበሩት ክቡር አምባሳደር ሽፈራው ጃርሶ የውሃና ኢነርጂ አውደርዕን ጎበኙ። ጷጉሜ 3/2015ዓ.ም ክቡር አምባሳደሩ ከጉብኝት በኋላ በሰጡን አስተያየት የአሁኑ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር በ1988ዓ.ም የውሃ ልማት ሚኒስቴር ሆኖ ሲቋቋም የመጀመሪያው ሚኒስትር ሆነው እንዳገለገሉ አስታውሰው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ዛሬ ላይ በዚህ ደረጃ ደርሶ በማየታቸው በጣም መደሰታቸውን ገልጸዋል። እንደ ሀገር ያለንን የውሃ ሀብት አውቀን ጥቅም ላይ ለማዋል እየተደረገ ያለው ጥረት በእጅጉ የሚበረታታ ነው ያሉት ክቡር አምባሳደሩ በተለይም ቆላማ አካባቢዎች ያለውን የከርሰ ምድር ውሃ አቅም ለመጠቀም የተኬደበት ስራ የሚያኮራ ነው ብለዋል። ውሃን ሳይጠቀም ያደገ ሀገር የለም የሚሉት ክቡር አምባሳደሩ ያለ ውሃ ኢንዱስትሪውም ሆነ ሌላው ልማት የትም ሊደርስ አይችልም።ደመናን በማበልጸግ ወደዝናብ የመቀየር ቴክኖሎጅ እንደ እስራኤል ያሉ ሀገራት 80 በመቶ የውሃ ሀብታቸውን ደመናን በማበልጸግ ቴክኖሎጅ ታግዘው እንደሚጠቀሙና እንደሀገርም በዘርፉ እየተሰራ ያለው ስራ አበረታች ነው ብለዋል። የውሃ ሀብትን በሚገባ አውቆ ሌሎች እንዲያውቁት አድርጎ መስራት ትልቅ ነገር ነው ያሉት ክቡር አምባሳደሩ፤ እነዚህ የተመለከትናቸው ቴክኖሎጅዎች በስፋት ህብረተሰቡ ጋር ደርሰው ከችግር እንዲወጡ ማድረግ የሁሉም ሀላፊነት ሊሆን እንደሚገባም ክቡር አምባሳደሩ ጠቁመዋል። በመጨረሻም አውደርዕዩ በቅርብ ጊዜ የአገራችን ብልጽግና ለማረጋገጥ ተስፋ የጣለ ሲሉም አስረግጠው ተናግረዋል።

Share this Post