ለንድፈ ሃሳብ ትምህርት አጋዥ የሆነ አውደ ርዕይ ነው። --- መምህራን

ለንድፈ ሃሳብ ትምህርት አጋዥ የሆነ አውደ ርዕይ ነው።-----------------------መምህራን መስከረም 9/2015ዓ.ም (ው.ኢ.ሚ) ሊጠናቀቅ አንድ ቀን ብቻ የቀረው የውሃና ኢነርጂ አውደርዕይ በበርካታ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቤት ተማሪዎችና መምህራን እየተጎበኘ ነው። በጉብኝቱ ያነጋገርናቸው የመድሐኒዓለም 2ኛ ደረጃ የኬሚስትሪ መምህር ብሩክ ገመቹ እንዳሉት ተማሪዎቻችን በትምህርት ቤታችን ቤተሙከራ ያላዩትን እና በንድፈሀሳብ ደረጃ ብቻ የሚያውቁትን በዚህ አውደርዕይ በማየታቸው ለትምህርታቸው ትልቅ አስተዋጽኦ አለው ብለዋል። በውሃ ዙሪያ ከ7ኛ ክፍል ጀምሮ ትምህርት ይሰጣል ያሉት መምህሩ ውሃ ከየት ይገኛል? እንዴት ይጣራል?ለምን አገልግሎት ይውላል የሚለውን ተማሪዎቹ በተግባር በማየታቸው ትልቅ ግብዓት አግኝተናል ብለዋል። ሚኒስቴሩ የሚሰራቸውን ዘርፈ ብዙ ስራዎች በአንድ ቦታ ማግኘቴ ብዙ እውቀት አግኝቻለሁ ያሉት መምህሩ የሌሎች ተቋማት ስራዎችም በዚህ መልክ ለእይታ ቢቀርቡ ለመምህራንም ሆነ ለተማሪዎች የሚሰጡት ጠቀሜታ የጎላ ነው ብለዋል። የህዳሴ ልደታ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሒሳብ መምህር ታደሠ ጉታ እንዳሉትም አውደ ርዕዩ ተማሪዎች የሰው ልጅ ምን ያህል በቴክኖሎጅ እንደረቀቀ የሚገነዘቡበትና ወደፊት ራሳቸውን የዚሁ አካል ለማድረግ የሳይንስ ትምህርት ላይ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ የሚያግዛቸው ሆኖ አግኝቸዋለሁ ብለዋል። አዲስ አበባ ውስጥ የዚህ አይነት ሙዚየም መኖሩም እጅግ በጣም እንዳስገረማቸው የነገሩን መምህር ታደሠ አውደርዕዩን እንዲጎበኙ እድሉን ያመቻቸላቸውን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አመስግነዋል። በእለቱ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ አቶ ጌትነት ጌጡ መምህራንንና ተማሪዎችን ተቀብለው ስለ ጉብኝታቸው መረጃ ሰጥተዋል

Share this Post