ለመማር ማስተማር ስራው ትልቅ ጠቀሜታ ያለው አውደ ርዕይ ነው። --ወ/ሮ ታጋይቷ አባቡ

ለመማር ማስተማር ስራው ትልቅ ጠቀሜታ ያለው አውደ ርዕይ ነው። ------------------------- ወ/ሮ ታጋይቷ አባቡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሊጠናቀቅ ቀናት ብቻ የቀረው የውሃና ኢነርጂ አውደ ርዕይ በተለያዩ ትምህርት ቤት ተማሪዎች፣ መምህራንንና የትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራን እየተጎበኘ ነው። ከጉብኝት በኃላ ያነጋገርናቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዋ ተማሪዎች ይህንን አውደርዕይ መጎብኘታቸው ክፍል ውስጥ በቲዎሪ የተማሩትን በተግባር ካዩት ጋር በማስተሳሰር ጥሩ ግንዛቤ እንዲይዙ እና በቀጣይም አዳዲስ የፈጠራ ስራዎችን ተግባራዊ እንዲያደርጉ ጠቀሜታው የጎላ ነው ብለዋል። አክለውም ተማሪዎች የነገ አገር ተረካቢ ዜጋ በመሆናቸው በሀገር ግንባታ ስራው ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ አገራችን የደረሰችበትን የቴክኖሎጅ እድገት እንዲያዩ ማድረጉ በቀጣይ የምንመኛትን ኢትዮጵያ ለማየት ወሳኝ ነው ብለዋል። አዲሱ ስርዓተ ትምህርት ተግባር ተኮር በመሆኑ የዚህ አይነቱ ሳይንሳዊ አውደ ርዕይ ተማሪዎች በየትምህርት ቤታቸው በቤተሙከራዎች ለሚሰሯቸው የምርምር ስራዎች በእጅጉ አጋዥ ናቸውም ብለዋል ም/ትምህርት ቢሮ ኃላፊዋ። በነገው እለትም ቀሪ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችን እንደሚያስጎበኙ መረጃ ሰጥተዋል።

Share this Post