17ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በአል በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ተከበረ።

17ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በአል በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ተከበረ። ህዳር 30/ 2015 - የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አመራሮች እና ሠራተኞች 17ኛውን የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን “ሕብረ ብሔራዊ አንድነት ለዘላቂ ሰላም!” በሚል መሪ ቃል አከበሩ፡፡ በበዓሉ አከባበር ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የክቡር ሚኒስቴር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ማሙሻ ሀይሉ ሀገራችን የብዙ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች መኖሪያ መሆኗን ገልጸው፤ በዘመናት በተለያዩ መስተጋብሮች ውስጥ አልፈን የመጣንና የጋራ እሴት ያለን ህዝቦች እንደሚሆናችን ህብረ ብሄራዊነታችን የበለጠ በማጠናከር ዘላቂ ሰላማችን ማረጋገጥ ይገባል ብዋል፡፡ የሚኒስቴሩ ህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ አቶ ጌትነት ጌጡ ሕብረ ብሔራዊ አንድነትና ለዘላቂ ሰላም በሚል የተዘጋጀውን ሰነድ አቅርበዋል፡፡ በሰነዱ የፌዴራሊዝም/የሕብረ ብሔራዊ ፌዴራሊዝም አረዳድ፤ ሕብረ ብሔራዊ አንድነት፤ሕብረ ብሔራዊ አንድነት እና ለዘላቂ ሰላም፤ ዘላቂ ሰላምና ሊያጋጥሙ የሚችሉ ተግዳሮቶች በሚሉ ርእሰ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ትንታኔ አቅርበዋል፡፡ በመድረኩ የዘንድሮው የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል «ኅብረ ብሔራዊ አንድነት ለዘላቂ ሰላም» በሚል መሪ ቃል ሲከበር ለህብረ ብሄራዊ አንድነታቸን ሰላም እጅግ ወሳኝ በመሆኑም ሀገራችን በእድገትና በልማት ጎዳና ለመጓዝ ያስችላት ዘንድ ልዩነታችንን በማጥበብ በአንድነት መንፈስ መጓዝ እንደሚገባን ተገልጿል፡፡

Share this Post